የደረቅ ወደብ አገልግሎት በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘ ማሻሻያ ተደረገለት

Date:

የኢትዮጵያ የደረቅ ወደቦች የጭነት አገልግሎት አሰጣጥን ወደ ላቀ የዲጂታል ምዝገባ ስርዓት የሚያሸጋግር መጠነ ሰፊ ማሻሻያ ተደረገለት።

የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማሕበር ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ታከለ ኡማ እንዳስታወቁት፤ ይህ አዲስ የበይነ-መረብ አሰራር ተቋሙ አገልግሎቱን ሙሉ በሙሉ ወደ አሃዛዊ (Digital) ስርዓት ለመቀየር የጀመረው ጥረት ወሳኝ አካል ነው።

አዲሱ ስርዓት ወደ ውጭ የሚላኩና ወደ ሀገር የሚገቡ ጭነቶችን አጠቃላይ ሂደት በአንድ ወጥ የዲጂታል መድረክ ከማስተሳሰሩም በላይ፣ ደኅንነቱ የተጠበቀ የመስመር ላይ ክፍያ እና የማረጋገጫ አገልግሎቶችን በውስጡ አካቷል። በተለይም ደንበኞች የጭነቶቻቸውን ጉዞ በቅርበት መከታተል የሚያስችላቸው (Tracking system) መገጠሙ የጭነት አያያዝ ውጤታማነትን በእጅጉ እንደሚያሳድገው ይጠበቃል።

ይህ ቴክኖሎጂ ተኮር እርምጃ በወደብ አገልግሎት ላይ የሚታየውን እንግልት በመቀነስ ለንግዱ ማኅበረሰብ የተቀላጠፈና ግልጽነት የሰፈነበት አሰራርን ለማቅረብ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ካናዳ ምዝገባም ሆነ ስምሪት አልተጀመረም

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መቀመጫውን ካናዳ ካደረገው "ፊውቸር ፊት ኢንተርናሽናል"...

የክቡር ዶክተር ጋሽ መሐሙድ አዲስ አልበም ለአድማጮች ሊደርስ ነዉ

ታዋቂው ድምፃዊ ክቡር ዶክተር አርቲስት መሐሙድ አሕመድ «ለታሪክ» የተሰኘውንና...

ሜታ ‘ፌስቡክ እና ኢንስታግራም በቀረበባቸው ክስ 18 ቢሊዮን ዶላር ለመክፈል ተስማማ

ግዙፉ የማኅበራዊ ሚዲያ ኩባንያ ሜታ በፌስቡክ እና በኢንስታግራም ምክንያት...