የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ አለምነሽ ደመቀ ለቋሚ ኮሚቴው ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን በበጀት ዓመቱ ከመደበኛ እና ከማዘጋጃ ቤቶች ገቢ ከ21 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ በ11 ወር ከ15 ቀናት ውስጥ ከ18 ቢሊዮን ብር በላይ የተሰበሰበ ሲሆን ከባለፈዉ ዓመት ተመሣሣይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከ5 ቢሊዮን ብር በላይ ብልጫ ማሳየቱ ተገልጿል፡፡
ከታክስ እና ንግድ ማጭበርበር እንዲሁም ገቢ ስወራ በ6 ዞኖች እና በክልል ማዕከል የተሰራ የኢንተለጀንስ ጥናት በ107 ታክስ ከፋዮች ላይ የማጣራት ሥራ ተሰርቶ 1 ሺህ 450 ታክስ ከፋዮች በተገኘ ሐሰተኛ ደረሰኝ 86 ሚሊዮን ብር ያልከፈሉትን ታክስ እንደከፈሉ በማድረግ በተመላሽ ስም ከየተቋማቱ መወሰዱ ታውቋል።ተቋማዊ የውስጥ ስጋትን ለመቀነስ የኦዲት ምርመራ በመስራት በቅድመ መከላከል ሰባት ዞኖችና ላይ በተሰራ ኦዲት ከ52 ጥራዝ ደረሰኝ 51 ሚሊዮን ብር የመንግስት ሀብት ማዳን ተችሏ::
በበጀት ዓመቱ 11 ወራት ከ15 ቀናት ከገጠር መሬት መጠቀሚያና ከእርሻ ሥራ ገቢ ግብር ብር ከ486 ሚሊዮን በላይ ለመሰብሰብ በዕቅድ ተይዞ ከ312 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰብስቧል።በበጀት ዓመቱ በ12 ማዕከላት ላይ አዲስ የሲግታስ ዝርጋታ ሥራ በመከናወኑ በክልሉ ከ64 የታክስ ማዕከላት ወደ 80 ዕድገት ማሳየቱ ተመላክቷል።
የክልሉ አስተባባሪ አካላት ለገቢ አሰባሰብ ሥራ የተለየ ትኩረት መስጠታቸው ፣ ጠንካራና ተከታታይ የክትትል ፣ ድጋፍና ግብረ-መልስ ስርዓት መዘርጋቱ ፣ የህግ ማዕቀፎችን በማሻሻል የታክስ መሰረቱን የማስፋት ስራዎች መከናወኑ እና ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት የገቢ መጠኑ 5.8 ቢሊዮን ብር በላይ ዕድገት ማሳየቱ በጠንካራ የተስተዋሉ ጉዳዮች መሆናቸውንም አክለዋል።
