በዚህ ወር ወደ ዋሽንግተን ያመራሉ
የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አል ሲሲ፣ የኢትዮጵያው ሕዳሴ ግድብ ከሁሉም የናይል ወንዝ ተፋሰስ አገራት ባለሙያዎችና ከአፍሪካ ኅብረት ተወካዮች በተውጣጣ “የባለሙያዎች ቡድን” ሥር እንዲተዳደር ፕሬዝዳንት ትራምፕ ኢትዮጵያን እንዲያሳምኑላቸው የመጠየቅ ፍላጎት እንዳላቸው ከምንጮቹ መስማቱን ጠቅሶ ዘ ናሽናል ድረገጽ ዘገበ።
ፕሬዝዳንት ሲሲ፣ በተያዘው ወር ወደ ዋሽንግተን አቅንተው ከፕሬዝዳንት ትራምፕ ጋር በግድቡና ሌሎች ቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለመወያየት ማቀዳቸውን ተዘግቧል።
ፕሬዝዳንት ሲሲ፣ የትኛውም የናይል ተፋሰስ አገር ሌሎች የተፋሰሱን አገራት ሳያማክር በናይል ወንዝ ላይ ግድብ እንዳይገነባ የሚያግድ “ቀጠናዊ ስምምነት” እንዲፈረም አሜሪካ ድጋፏን እንድትሠጥ የመጠየቅ ፍላጎት እንዳላቸውም ምንጮች እንደነገሩት ዘገባው ጠቅሷል።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ በመጀመሪያው የሥልጣን ዘመናቸው፣ ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ በግድቡ ውሃ ሙሌትና አስተዳደር ዙሪያ አስገዳጅ ስምምነት እንዲፈርሙ ያቀረቡትን ረቂቅ የስምምነት ሰነድ ኢትዮጵያ ውድቅ ማድረጓን አስታውሳለች፡፡
ዋዜማ
