በነፃ ሀሳብና በሰከነ መንፈስ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን እናድምቅ በሚል መርህ ለ14 ዓመታት ተወዳጅነት ያተረፈው “ጦቢያ” በሆፕ ፎር ኦል በተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት አዘጋጅነት በአውሮፓ ከተሞች በአምስተርዳም ኦገስት 9 ፣ ኑረንበርግ ኦገስት 16 ፣ ፍራንክፈርት ኦገስት 23 ፣ኮለን ኦገስት 30 ፣ ሙንሽ ሰብቴምበር 5 አዘጋጅተዋል ።
መቀመጫው በጀርመን ሀገር ያደረገው ሆፕ ፎር ኦል ለረጅም ዓመታት የኢትዮጵያ ተማሪዎች በማገዝ መጠነ ሰፊ ስራ እየሰራ የሚገኝ ሲሆን የዚህም መድረክ አላማ በተለይ ለወጣት ሴት ተማሪዎች የንፅህና መጠበቂያ ተደራሽ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።
እየተዝናናችሁ ወገኖቻችሁን ታግዙ ዘንድ መልእክቱን አስተላልፏል ።
