▪️አስራ ሁለት የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት አባላት ድጋፍ በሰጡበትና ሩሲያ፣ ቻይና እና ፓኪስታን ድምጸ ተዓቅቦ ባደረጉበት ውሳኔ ሰላም አስከባሪ ኃይሉ እስከ ሚያዝያ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ እንዲቆይ ፀድቋል።
▪️በአሜሪካ የቀረበው ረቂቅ ውሳኔ በጾታ፣ በአየር ንብረት ለውጥ እና በሰብዓዊ መብቶች ዙሪያ በተፈጠሩ አለመግባባቶች ለተወሰነ ግዜ ተራዝሞ ነበር።
🇷🇺 ከድምጽ አሰጣጡ በኋላ የሩሲያ፣ የቻይና እና የፓኪስታን ተወካዮች ትችቶችን አሰምተዋል። ሩሲያ የተባበሩት መንግሥታት የደቡብ ሱዳን ተልዕኮን ሥራ ብትደግፍም፤ አሜሪካ በደቡብ ሱዳን መንግሥት ላይ “ጫና እያሳደረች ነው” ስትል ከሳለች።
👉 በተመሳሳይ ቻይና ውሳኔው “በመሬት ላይ ያለውን እውነታ” ያላንፀባረቀ “ከመጠን በላይ ጫና” ፈጥሯል ስትል ተከራክራለች።
