የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ መልቀቂያ ፈተና በዛሬው ዕለት መሰጠት ተጀመረ

Date:

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ከዛሬ ሰኔ 8 እስከ ሰኔ 10/2018 ዓ.ም በተለያዩ የፈተና ጣቢያዎች መሰጠት ጀምሯል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ክብር ዶክተር ዘላለም ሙላቱ እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በዳግማዊ ሚኒሊክ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመገኘት ፈተናውን በይፋ አስጀምረዋል።

👉🏼 85,017 የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች በከተማ ደረጃ ፈተናውን ይወስዳሉ።

👉🏼 በአጠቃላይ በ199 የፈተና ጣቢያዎች ፈተናው እየተሰጠ ይገኛል።

ፈተናው ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በየደረጃው የኮማንድ ፖስት አደረጃጀት ተዋቅሮ የጸጥታ አካላትና ልምድ ያላቸው አስፈጻሚዎች ተመድበዋል።

በከተማ አስተዳደሩ የተማሪዎች የምገባ አገልግሎት፣ የዩኒፎርምና የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉ ለውጤት መሻሻል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጉ ተገልጿል። ዘንድሮም ከተደረገው ዝግጅት አንጻር የተሻለ ውጤት እንደሚጠበቅ ተጠቁሟል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአህጉሪቱን የርስ በርስ ንግድ ልውውጥ 250 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ታቀደ

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ዋና ፀሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ...

በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦች ክፍያ መፈጸም አይጠበቅባቸውም

አሜሪካ እና ኢራን በተስማሙበት የመግባቢያ ሰነድ መሠረት በሆርሙዝ ወሽመጥ...

እስራኤል ጦሯ በደቡብ ሊባኖስ እንደሚቆይ አስታወቀች

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ እንደተናገሩት፤ በአሜሪካ እና በኢራን...

ኧረ ፋታ ስጡን?!

መንግስት ግን" ምን ሁኑ ?" ሊለን ነው :: አጀንዳ...