ደቡብ ሱዳን በሁለት ዓመታት ልዩነት ሦስተኛ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሾመች

Date:

ደቡብ ሱዳን በሁለት ዓመታት ልዩነት ሦስተኛ የውጪ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ተሾመላት። የሀገሪቱ ፕሬዝደንት ሳልቫ ኪር ሚያርዲት አዲስ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር የሾሙት ከተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝደንት ሪየክ ማቻር የገቡበት የፖለቲካ ውዝግብ ሀገሪቱን ወደ የርስ በርስ ጦርነት ሊከታት ይችላል የሚል ሥጋት ባየለበት ወቅት ነው።

አዲሱ የደቡብ ሱዳን የውጪ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር አምባሳደር መንደይ ሰማያ ኩምባ ትላንት አርብ ፕሬዝደንቱ በተገኙበት ቃለ-መሐላ ፈጽመዋል። አምባሳደር መንደይ የደቡብ ሱዳንን የውጪ ጉዳይ ፖሊሲ እንዲያራምዱ እና የሀገሪቱን ገጽታ እንዲያሻሽሉ ትዕዛዝ ተሰጥቷቸዋል።
አምባሳደር መንደይ ከሹመታቸው በፊት በምክትል የውጪ ጉዳይ ሚኒስትርነት ሲሰሩ ነበር። የቀድሞው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ረመዳን አብደላ ጎክ ከኃላፊነታቸው ለምን እንደተሻሩ የተባለ ነገር የለም።

ረመዳን አብደላ ጎክ በውጪ ጉዳይ ሚኒስትርነት ደቡብ ሱዳንን የመሩት ለአንድ ዓመት ገደማ ብቻ ነው። ረመዳን አብደላ በሚያዝያ 2016 በውጪ ጉዳይ ሚኒስትርነት የተሾሙት ዶክተር ጄምስ ፒቲያ ሞርጋን ከኃላፊነቱ ከተባረሩ በኋላ ነበር።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የእግር ኳስ ዳኝነት በኢትዮጵያ

ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) ግዮን መጽሔት :- እግር ኳስ...

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...

አገር እንዲህ ዓይንህን ለአፈር ይባላል?

በተጀመረው የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ መሸነፏን ተከትሎ አፍሪካ...