ገንቢ ውይይት ለዴሞክራሲ ግንባታ

Date:

ግዮን መጽሔት :- ምርጫ መሪዎችን የመምረጥ ሂደት ብቻ ሳይሆን፣ እንደ ማኅበረሰብ የምንወያይበት መድረክም ነው፡፡ ወጣቶች በአካባቢያቸው በሚደረጉ የፖለቲካ ስብሰባዎችና ክርክሮች ላይ ሲሳተፉ፦

• ጥያቄዎችን ማዘጋጀት፦ በአካባቢያችሁ ስላለው የትምህርት ጥራት፣ ስለ ሥራ ዕድል ፈጠራ፣ ስለ ሰላም እና ስለ ልማት ዕቅዶች ዕጩዎችን በጥልቀት ጠይቁ፡፡ ውይይቱ በግለሰቦች ማንነት ላይ ሳይሆን በፖሊሲና በሥራ ዕቅድ ላይ እንዲያተኩር አድርጉ፡፡


• የጋራ እሴቶችን መፈለግ፦ በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ልዩነት ቢኖርም፣ ሁሉም የሚስማሙባቸው አገራዊ ጉዳዮች አሉ፡፡ ወጣቶች እነዚህን የጋራ ነጥቦች በማጉላት፣ ፖለቲካው ከከረረ ልዩነት ወጥቶ ወደ የጋራ መፍትሔ እንዲያመራ ግፊት ማድረግ ይችላሉ፡፡

  1. የሰላም አምባሳደርነት ኃላፊነት

  2. ወጣቶች የአገሪቱ የሰላም ዘቦች ናቸው፡፡ በምርጫ ወቅት የሚከሰት ማንኛውም አለመረጋጋት ቀጥተኛ ሰለባው ወጣቱ እንደሆነ የታሪክ ትምህርታችን ነው፡፡ ስለዚህ፦

  3. • የሐሰት መረጃዎችን መከላከል፦ ግጭት እንዲቀሰቀስ የሚያደርጉ የሐሰት ወሬዎችንና የተዛቡ መረጃዎችን ባለማሰራጨትና እውነታውን በማጣራት የማኅበረሰቡን ሰላም መጠበቅ ይገባል።

  4. • አርአያነት ያለው ተግባር፦ በሰልፎች፣ በስብሰባዎችና በሕዝባዊ መድረኮች ላይ ወጣቶች በዲሲፕሊንና በሥርዓት በመንቀሳቀስ ለሌላው የኅብረተሰብ ክፍል አርአያ መሆን አለባቸው።

  5. ማጠቃለያ
    ውድ ወጣቶች፤
    የዘንድሮው ምርጫ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ቁልፉ በእጃችሁ ነው። ልዩነቶቻችንን በውይይት፣ ቅሬታዎቻችንን በሕጋዊ መንገድ፣ ፍላጎቶቻችንን ደግሞ በምርጫ ካርዳችን የምንገልጽበት ባህል ማሳደግ አለብን።

  6. የማይስማማችሁን ሐሳብ በሰላም ማዳመጥና በሐሳብ መሞገት የዴሞክራሲያዊ ብስለት ጥቆማ ነው። ይህ ምርጫ ተካሂዶ ያልፋል፤ እኛ ግን እንደ አንድ ሕዝብና እንደ አንድ አገር አብረን መኖራችንን እንቀጥላለን። በመሆኑም በምርጫው ሂደት ውስጥ የምናሳየው እያንዳንዱ እንቅስቃሴ ነገ የምንገነባትን ኢትዮጵያ የሚወስን መሆኑን አንዘንጋ።

  7. ለሰላም ቅድሚያ እንስጥ፣ ለሐሳብ ልዩነት ዕውቅና እንስጥ፣ ለዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ በጋራ እንቁም!

  8. ሰላማዊ ምርጫ ለተረጋጋችና ለበለፀገች ኢትዮጵያ!

ይህ ጽሑፍ የተዘጋጀው በወጣቶች እና ባህል ልማት ፋውንዴሽን (Youth and Cultural Development Foundation – YCDF) ከ UNDP ጋር በመተባበር ነው።

የወጣቶች እና ባህል ልማት ፋውንዴሽን በኢትዮጵያ ውስጥ የወጣቶችን ሁለንተናዊ አቅም በመገንባት፣ ባህላዊ እሴቶችን በማሳደግ፣ የሰላም
ግንባታ ሥራዎችን በማስፋፋት እና የወጣቶችን ንቁ ዴሞክራሲያዊ ተሳትፎ በማጎልበት ላይ በትኩረት የሚሠራ ገለልተኛ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት ነው።

ድርጅቱ ወጣቶች በሀገር ግንባታ ሒደት ውስጥ ገንቢ ሚና እንዲጫወቱ ግንዛቤ በመፍጠርና አቅማቸውን በማጎልበት የላቀ አስተዋጽዖ በማድረግ ላይ ይገኛል።

ግዮን መጽሔት ቅጽ 8 ቁጥር  233 ግንቦት 2018 ዓ.ም

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በ2026 የዓለም ዋንጫ ላይ ለተለያዩ ብሔራዊ ቡድኖች የሚጫወቱ ወንድማማቾች

የ2026 የፊፋ የዓለም ዋንጫ ከመላው ዓለም የተውጣጡ ምርጥ ተጫዋቾችን...

ኢንፊኒቲ ለቤትና ለመኪና መግዣ ብድር እየሰጠ እንደሚገኝ አስታወቀ

ኢንፊኒቲ ኃላፊነቱ የተወሠነ መሠረታዊ የቁጠባ እና ብድር ኀብረት ሥራ...

የአዲሱ የወንጀል ህግ ስነ-ስርዓት የእርማት ስራዎች ሳይጠናቀቁ በሥራ ላይ እየዋለ ነው

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ላለፉት 64 ዓመታት...

ናይጄሪያው ዩናይትድ ካፒታል በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የውጭ ኢንቨስትመንት ባንክ ፈቃድ አገኘ

​የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን በሀገሪቱ የካፒታል ገበያ ታሪክ ለመጀመሪያ...