ጉባኤው ለቀጣዩ ትውልድ ጠንካራና አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት እንደሆነ የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዐያ ተናገሩ

Date:



ኢትዮጵያ በሀሳብ ልዩነትና በአለመግባባት ውስጥ ማለፏ እንደማይካድ የገለጹት የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዐያ፤ እነዚህ የዘመናት የሥርዓትና የፖለቲካ ጥያቄዎች ሀገሪቱን እየፈተኑ ይገኛሉ ብለዋል።

ይህ ጉባኤ ለቀጣዩ ትውልድ ጠንካራና አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት እንደሆነ አንስተው፤ ጉባኤው በወደፊት ዕጣ ፈንታችን ላይ እንድንስማማና እንድንወስን ዕድል የሚሰጥ እንደሆነ ተናግረዋል።

ኮሚሽኑ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ በርካታ ፈታኝ ሁኔታዎችን በመቋቋም ዛሬ ላይ መድረሱን ጠቅሰው፤ የአሠራር ሥርዓት በመዘርጋት የምክክር ሂደቱ ሕጋዊነትና ተዓማኒነትን በጠበቀ መልኩ እንዲቀጥል ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል።

በተጨማሪም ለምክክር ሂደቱ ተሳታፊዎችን የመለየት፣ አጀንዳ የመለየትና የማሰባሰብ እንዲሁም ግንዛቤ የመፍጠር ሥራዎች መከናወናቸውን አስረድተዋል።

“11 ኮሚሽነሮች፣ ከባለሙያዎችና ከድጋፍ ሰጪዎች ጋር በመሆን ዛሬ ላይ ደርሰናል” ያሉት የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዐያ፤ ወደ መጨረሻው ምዕራፍ ላይ ስንደርስ ግን ሁለት ትላልቅ ሰዎችን አጥተናል በማለት አቶ ዘገየ አስፋው እና የኮሚሽኑ አማካሪ የነበሩትን አዛዥ ይርጋ ገብሬን አስታውሰዋል።

ለአራት ዓመታት በሂደት ላይ የቆየው ሀገራዊ ምክክር ጉባዔ በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል መካሄድ የጀመረ ሲሆን፣ በምክክር ጉባኤው ላይ ከመላው ኢትዮጵያ የተወጣጡ ከ4 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ10 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ ጥቅምት 12 ቀን 2019...

ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ የፕላቲንየም ብራንድ የማስተር ካርድ ይፋ አደረጉ

ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ደንበኞች የፕሪሚየም...

የአሜሪካ የደህንነት ኃላፊ ኢራንን አስጠነቀቁ

ቡሔራዊ ደህንነት ዳይሬክተር ጄይ ክላይተን አርብ ዕለት ኢራን በውጭ...

ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ  በአመት ከ1.1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ታጣለች

85 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ በግብርናው ዘርፍ የተሰማራ ሲሆን...