ለማስፋፋት የ37 ሚ. ዶላር ድጋፍ አደረገ
ጉግል በአፍሪካ የኤ.አይ ጥናትና ምርምርን ለማጠናከር፣ የአፍሪካን ቋንቋዎች በቴክኖሎጂ ለመደገፍ፣ የምግብ ሥርዓትን ለማስተካከልና ዲጂታል ክህሎትን ለማስፋፋት ያለመ የ37 ሚሊየን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ይፋ አድርጓል፡፡
ከድጋፍ ገንዘቡ 25 ሚሊዮን ዶላር የሚሆነው ቴክኖሎጂውን በመጠቀም የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚውል ይሆናል፡፡
በዚህ ድጋፍ ተመራማሪዎችና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት በመቀናጀት ኤ.አይን በመጠቀም ረሀብን ለመከላከልና የአፍሪካን የምግብ ሥርዓት ለማሻሻል ታቅዷል፡፡
የአፍሪካን ቋንቋዎች በቴክኖሎጂ ማሳደግ ብሎም የኤአ.ይ ስታርታፖችን የገንዘብ አቅም ማጠናከር የዚህ ድጋፍ አካል መሆናቸውን ኢኮኖሚክ ታይምስ ዘግቧል፡፡
