ፕሮሞተር እና ጋዜጠኛ አብርሃም ግዛው ከ15 ዓመት በላይ የተለያዪ ሁነቶችን ሲያዘጋጅ የነበረ በርካታ ብራንድ አምባሳደሮችን ሲያፈራርም የቆየ የሚዲያ ባለሙያ መሆኑ ይታወቃል። ዛሬም ለአንድ ዓመት የሚቆይ በ1.5 ሚሊየን ብር የአምባሳደርነት ስምምነት ከፍላይ አዲስ ጋር ተፈራርሟል።
ፍላይ አዲስ ትራቭል ሶሉሽን ከሚመለከተው ሚኒስቴር መ/ቤት ሕጋዊ እውቅና በማግኘት ላለፉት አራት ዓመታት አውሮፓ፣ ፖላንድ፣ ቱርክ፣ ጣሊያን፣ ካናዳ፣ ሩሲያ እና ሌሎች በርካታ ሀገራት ለትምህርት፣ ለሥራና ለሕክምና እንዲሁም ለጉብኝት ጉዞ ለሚያደርጉ ዜጎች ሕጋዊ ቪዛና የጉዞ እንዲሁም የማማከር አገልግሎት በመስጠት የሚታወቅ ተቋም ነው።
ከዚህም ጋር በተያያዘ በአሁን ሰዓት እነዚህኑ የቪዛ፣ የጉዞና የማማከር አገልግሎቶችን ይበልጥ በማዘመንና በማስፋት ሀገራት በተጨማሪ በሌሎች ሀገራትም ዜጉች አገልግሎቱን ማግኘት እንዲችሉ ከዳሽን ባንክ ጋር በመተባበር የዱቤ አገልግሎት በመስጠት ሕብረተሰቡ በሚሄዱባቸው ሀገራት ሁሉ ለሚያስፈልጓቸው የጉዞ፣ የቪዛና ሌሎች አገልግሎቶቹን በዱቤ ማግኘት እንዲችሉ የሚያመቻች ድርጅት ነው ከጋዜጠኛ አብርሃም ግዛው ጋር መፈራረማችን ስራችንን የበለጠ ተደራሽ ያደርገዋል ሲሉ ተናግረዋል።
