በኢትዮጵያ አዘጋጅነት ለአራት ቀናት በአዲስ አበባ ሲካሄድ የቆየው 22ኛው የምስራቅ አፍሪካ የኃይል ትስስር የሚኒስትሮች ምክር ቤት እና 37ኛው የአስተባባሪ ኮሚቴ አስቸኳይ ልዩ ጉባዔ ዛሬ ተጠናቋል።
ግብፅና ሊቢያ ጨምሮ 13 አባል ሀገራት ያሉት ትስስሩ የመበታተን አደጋ የተጋረጠበት በመሆኑ ነው አስቸኳይ ስብሰባ ማድረግ ያስፈለገው፡፡
አባል ሀገራቱን ከመበታተን ለመታደግ የህግ ማዕቀፎችን በማሻሻልና ማጠናከር ማስፈለጉን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ ገልጸዋል።
በጉባዔው አዲስ የሚመሰረተው የኤሌክትሪክ ኃይል የገበያ ማዕከል ዋና መቀመጫን ለመወሰን ውይይት ተደርጓል፡፡
በዚህ አጀንዳ ኢትዮጵያ ከድርጅቱ አባል ሀገራት ብቸኛ የኃይል አቅራቢ እንደመሆኗ ለአራት ቀናት በዘለቀው የትስስሩ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ከፍተኛ ሙግት ማካሄዱ ተገልጿል፡፡
በተለይም ከግብፅ ጋር የገበያ ማዕከሉ ኢትዮጵያ መሆን አለበት በሚለው ሃሳብ ከፍተኛ ሙግት መደረጉን ኢነርጂ ሃብታሙ ኢተፋ ገልፀዋል።
በዚሁ ጉዳይ የግብፅ ተወካዮች ማዕከሉ ወደ ካይሮ ካልሆነ በሚል የያዙት አቋም ከኢትዮጵያ ጋር ከመግባባት ሳይደርሱበ ጉባዔው ተጠናቋል።
