ምስረታውን ነሐሴ 17 ቀን 1990 ዓ.ም ያደረገው ጤና ልማትና ፀረ ወባ ማህበር “ወባን በእኛ ሀብት፣በእኛ እውቀትና ጉልበት እናጠፋለን” በሚል መሪ ቃል 27ኛ ዓመት ምስረታውን አክብሯል።
የጎጃም አካባቢን ትኩረት አድርጎ የተነሳው ማህበሩ በአሁኑ ጊዜ በ10 ክልሎች ላይ ሌሎች ሶስት ድርጅቶችን አቅፎ በወባ ላይ ትኩረት ያደረገ ፕሮጀክት በመተግበር ላይ ይገኛል።
ጤና ልማትና ፀረ-ወባ ማህበር በ10 ክልሎች በሚገኙ 222 ወረዳዎች ፕሮጀክት ለመተግበር ዝግጅቱን አጠናቆ በይፋ ስራ መጀመሩን አስታውቋል።
ጤና ልማትና ፀረ ወባ ማህበር በአሁኑ ጊዜ 260 ሺ አባላት ያሉት ሲሆን በቀጣዮቹ ዓመታት የማህበሩ አባላት ወደ 1 ሚሊየን ለማድረስ እቅድ ይዞ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል ሲሉ የጤና ልማትና ፀረ ወባ ማህበር መስራች እና ሰብሳቢ አበረ ምህረቴ ተናግረዋል።
ሁሉም ሰው በዓመት 1200 ብር ለፀረ ወባ ማህበር የገንዘብ መዋጮ በማድረግ እና አባል በመሆን ተረባርበን ወባን ማጥፋት አለብን ሲሉ አበረ ምህረቴ ጥሪ አቅርበዋል።
ጤና ልማትና ፀረ-ወባ ማህበር በ10 ክልሎች በሚገኙ ከፍተኛ የወባ ጫና ባለባቸው 222 ወረዳዎች “ትምህርት ቤት እና ማህበረሰብ አቀፍ ማህበራዊ የባህሪ ለውጥ የወባ በሽታ ጫናን ለመቀነስ በኢትዮጵያ” የተሰኘ ፕሮጀክት ለመተግበር ዝግጅቱን አጠናቆ በይፋ ስራ መጀመሩን ብስራት ሬድዮ ሰምቷል።
