ፍቅረሰላም አጠቃላይ ሆስፒታል  የISO 15189 የህክምና  ላቦራቶሪ   የብቃት ማረጋገጫን አገኘ

Date:

የአለም አክሪዲቴሽን ቀን ለ16ኛ ቀን በተከበረበት ዕለት ከተመሠረት 25 ዓመቱን  ያስቆጠረው ፍቅረሰላም አጠቃላይ ሆስፒታል ከኢትዮጵያ አክሪዲቴሽን አገልግሎት የISO 15189 2022 የህክምና ላቦራቶሪ የጥራት አስተዳደር ሥርዓት የብቃት ማረጋገጫን አግኝቷል።

የሆስፒታሉ መስራች እና ባለቤት እንዲሁም ስራ አስኪያጅ የሆኑት ደ/ር ፍቅረማሪያም ጉድታ እንደተናገሩት ይህ ምዕራፍ ሆስፒታሉ ከ250 በላይ አለም አቀፍ የላቦራቶሪ የጥራት መስፈርቶችን ማሟላቱን የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል።

በተጨማሪም ለታካሚዎች የላቀውን እና ደህንነቱ የተጠበቀ አገልግሎት ለመስጠት ሆስፒታሉ ያሳየውን ቁርጠኝነት የሚያንፀባርቅ ነው ብለዋል።

ሲስተር ቅድስት ኃይለማሪያም የሆስፒታሉ የጥራት አስተዳደር የሥራ መሪ የላቦራቶሪ የጥራት አስተዳደር ስርዓት በሆስፒታል ላቦራቶሪ ውስጥ ሁሉንም ሂደቶች መደበኛ እና ከፍተኛ ጥራት ያለው እንዲሆን የሚያደርግ ሆኖ የተዋቀረ አስተዳደራዊ ስርዓት መሆኑን ተናግረዋል።ይህም ሥርዓት በተለይ በዓለም አቀፍ መስፈርቶች (እንደ ISO 15189 መሠረት የተዘጋጀ ነው።

ሆስፒታሉ ያሟላቸው ቁልፋ የጥራት መስፈርቶች የላቦራቶሪው የጥራት ቁርጠኝነት ፣ሰነድ አስተዳደር(  Control document)፣ የላቦራቶሪ ባለሙያዎች ብቃት ማረጋገጥ፣ የመሳሪያዎች ብቃትን ማረጋገጥ ፣ የናሙና አያያዝ፣ የናሙና አውሰድ፣ ማጓጓዝ፣ ማከማቸት እና መለየት፤ የውጤት   ትክክለኛነትና አስተማማኝነት እና ሌሎችም እንደሚገኙበት ለማወቅ ተችሏል።

ሆስፒታሉ በቀጣይነትየጥራት አፈፃፀሙን በየግዜው መቆጣጠር የውጪ ግምገማዎችን በየወሩ በማጠናከር እና አክሪዲቴሽኑ ዘላቂ ሆኖ እንዲቆይ እንደሚያደርግ የሆስፒታሉ የበላይ ኃላፊዎች ይናገራሉ።

አቶ እንዳለው መኮንን  የኢፌድሪ ንግድና ቀጠናዊ ትስስር  ሚኒስቴር  የጥራት ሬጉላተሪ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ባደረጉት ንግግር የኢትዮጵያ አክሪዲቴሽን አገልግሎት  ያደረገው ተቋማዊ ግንባታ አስደናቂ መሆኑን ገልፀው ለተወዳዳሪነት አክሪዲቴሽን መሠረታዊ መሆኑን ተናግረዋል።

እንደ ሚኒስትር ዲኤታው ገለፃ ኢኖቬሽን በዛሬ ዘመን ዋና ጉዳይ መሆኑን  ገልፀው   ተቋማትም በቴክኖሎጂ ታግዘው ሥራቸውን በጥራትና በተወዳዳሪነት መሥራት አለባቸው ብለዋል።እንደ አገር ዘላቂነት ላይ መስራት ወሳኝ መሆኑን ገልፀው ሁሉም ተቋማት በአንድ ልብ የጀመሩትን አጠናቀው በጥራት ሊሠሩ ይገባል ብለዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው ዕውቅና ያገኙ ተቋማትን  የእንኳን ደስ ያላችሁ  መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን ከዚህ  በበለጠ መሥራት እንዳለባቸው አመላክተዋል።

የኢትዮጵያ አክሪዲቴሽን አገልግሎት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር195/2003 መቋቋሙ ይታወቃል።አገልግሎቱ ተጠሪነቱ ለንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሆኖ በህክምና iso 15189 እና በፍተሻ ላቦራቶሪiso/ ies 17028፣ በሰርተፊኬሽንiso/ies 17065 እና iso/ies 17024 እንዲሁም በኢንስፔክሽን iso/ies 17020 ሥራ ላይ ለተሠማሩ የተስማሚነት ምዘና ተቋማት ብቃታቸውን በማረጋገጥ የአክሪዲቴሽን አገልግሎት በመስጠት የተቋማቱን አገልግሎቶች እና የሚያመርቱት ምርቶች ላይ ተጠቃሚውም ሆነ አምራቾች በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር ተቀባይነት እንዲኖራቸው ለማድረግ አለም አቀፍ የአሠራር ሥርዓትን ዘርግቶ በተጠናከረ መልኩ አገልግሎቱን እየሰጠ ይገኛል።

ተቋሙ በአለም ለ19ኛ ጊዜ በአገራችን ደግሞ ለ16ኛ ጊዜ የተከበረውን የአለም የአክሪዲቴሽን ቀን ዘንድሮ ሰኔ 15 2018 “አክሪዲቴሽን ለፈጠራ  እምነት እና ዘላቂነት በሚል ቃል  በዓሉን አክብሯል። በዕለቱም ፍቅረሰላም ሆስፒታልን ጨምሮ ሌሎች ተቋማትም የምዘና ብቃት ማረጋገጫ እንዳገኙ ታውቋል።

“ወርቃማ ልቦች ፣ አገልጋይ እጆች !” በሚል መርህ ከክሊኒክ አንስቶ እስከ አጠቃላይ ሆስፒታል 25 ዓመታት የዘለቀው ፍቅረሰላም አጠቃላይ ሆስፒታል ለ250 ሰዎች የሥራ ዕድል የፈጠረ ነው።

ፍቅረሰላም አጠቃላይ ሆስፒታል በዋናነት በ3 ነገሮች ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሠራ የተገለፀ ሲሆን  የመጀመሪያው ቅድመ መከላከል ላይ በትኩረት ይሠራል። እንክብካቤ በማድረግና ማከም ደግሞ ሁለተኛና ሦስተኛ ትኩረቱ  ነው ።

ፍቅረሠላም አጠቃላይ ሆስፒታል አለም አቀፍ ደረጃቸውን በጠበቁ ቴክኖሎጂዎችና በሙያቸው አንቱ በተባሉ ሙያተኞች የተሟላ የህክምና አገልግሎት ለህብረተሰቡ በመስጠት ላይ የሚገኝ ሲሆን የውስጥ ደዌ ህክምና ፣ የማህፀንና ፅንስ ክትትል፣ የህፃናት ህክምና ጠቅላላ ቀዶ ህክምና ፣ ሆድ ሳይከፈት ቀዶ ህክምና፣ የአእምሮ ህክምና፣ የደምና የደም ካንሰር፣ ፕላስቲክ ሰርጀሪና የመሳሰሉትን ህክምናዎች ይሰጣል።

ፍቅረሠላም  አጠቃላይ ሆስፒታል በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ሲኤምሲ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ፊትለፊት ከጋስትሞል ጀርባ የሚገኝ የህክምና ተቋም ነው።

ይህን የሚድያ ይዘት እና ሁነት በማስተባበር  ተወዳጅ ሚድያ እና ኮምዩኒኬሽን  ኃላፊነቱን ተወጥቷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እስከ አምስት ዓመት እስራት የሚያስቀጡ የመረጃ ነጻነት አዋጅ ጸደቀ

ለ15 ዓመታት በስራ ላይ ከቆየው “የመገናኛ ብዙኃንና የመረጃ ነፃነት...

በደቡብ አፍሪካ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን የተላለፈ ማስጠንቀቂያ

በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኢምባሲ በሀገሪቱ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ እየተከታተለና...

በበጀት አመቱ 22.9 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ለማቅረብ እየተሠራ ነው

ከታቀደው 22 ነጥብ 9 ሚሊዮን ዶላር ኩንታል እስካሁን  20...

በቬንዝዌላ በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ የ32 ሰዎች ህይወት አልፏል

በቬንዙዌላ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀ ሲሆን 7.2 እና 7.5...