የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በዓሉን አስመልክቶ በዛሬው እለት በሰጠው መግለጫ በዓሉ የፊታች ሐሙስ ነሐሴ 29 ቀን 20217 ዓ.ም በአንዋር መስጊድ ይከበራል ብሏል።
የልደት በዓሉ ሲከበር ሁሉም የሀይማኖት ተቋማት ለሀገር ሰላም መስፈን በጋራ የሚያከብሩበት ሊሆን ይገባል ብሏል ጠቅላይ ምክር ቤቱ።
በተጨማሪም ሰላምን፣ መቻቻልን፣ ከሌሎች ጋር ተከባብሮ የመኖር እና የአንድነት እሴቶችን ማስታወስ የበዓሉ አካል ሊሆን እንደሚገባ በመግለጫው ተነስቷል።
ወቅቱ በርካታ ድጋፍ የሚሹ ዜጎች ያሉበት በመሆኑ እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን ማገዝ የህዝበ ሙስሊሙ ተግባር ሊሆን እንደሚገባ የጠቅላይ ምክር ቤቱ የስራ አስፈፃሚ አባልና የሴቶች እና ወጣቶች ዘርፍ ተጠሪ ሺህ አብዱል ሀሚድ አህመድ አሳስበዋል።
