(ሚያዝያ 13/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ 10ኛዉን ከተማ አቀፍ የሳይንስ የፈጠራ ስራ አውደ ርዕይ ከሚያዚያ 16-18/2017 ዓ.ም ድረስ “በፈጠራ ስራ የተካነ ትጉህ ትውልድ ለሀገር ብልጽግና!” በሚል መሪ ሀሳብ ከፍተኛ የመንግስት የሰራ ሀላፊዎች ፣ የትምህርት አመራሮች ፣ የትምህርት ባለድርሻ አካላት ፣ የትምህርት ባለሙያዎች ፣ መምህራንና ተማሪዎች በተገኙበት በወዳጅነት ፓርክ ያከናውናል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ እያከናወናቸው ያሉ የትምህርት ልማት ስራዎች ፍራቸውን በሳይንስና የፈጠራ ስራ ላይ የምናይበት ብሎም በዓውደ ርዕዩ ላይ የምንመለከታቸው የተማሪዎችና የመምህራን የፈጠራ ስራዎች የሀገራችንን የፈጠራ ስራ ወደ ፊት ከፍ የሚያደርጉ እንደሚሆኑ ይታመናል፡፡
10ኛዉን ከተማ አቀፍ የሳይንስ የፈጠራ ስራ አውደ ርዕይ ለትውልድ ግንባታ የተሰጠውን የላቀ ትኩረት በተጨባጭ በፈጠራ ስራው ከፍ ብሎ በተግባር የሚታይበት ፤ ችግር ፈቺ ትጉ ትውልድ የሚገነባበትና ለአዲስ አበባ ሁለንተናዊ ዕድገትና ብልጽግና የሚሰሩ ጥበበኛ ወጣቶችን የምናይበት መድረክ እንደሚሆንም ይጠበቃል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
