የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዛሬው ዕለት ለባንኩ ከቀረቡ የግሉ ዘርፍ የውጭ ምንዛሪ ጥያቄ ማመልከቻዎች ውስጥ 505ቱን በማጽደቅ ወይም 81 በመቶ ለሚሆኑት ጥያቄዎች ምላሽ መስጠቱን አስታውቋል።
የ121 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸውን የተለያዩ የውጭ ምንዛሪ ኣይነቶች ለተለያዩ ፍላጎቶች መፍቀዱን ገልጿል።
ይህ ፈቃድ ማዳበሪያ፣ ነዳጅ እና ሌሎች የገቢ እና የአገልግሎት ክፍያ ፍላጎቶች በየቀኑ እና በመደበኛነት ከሚደረገው የውጭ ምንዛሪ ድጋፍ በተጨማሪእንደሆነ ነው ያስታወቀው ።
የውጭ ምንዛሪ ፈቃድን ከደንበኞች ፍላጎት እና ከአገሪቱ ስትራቴጂካዊ ቅድሚያዎች ጋር አጣጥሞ በመደበኛነት ምላሽ እንደሚሰጥ ባንኩ በማህበራዊ ድረገጹ ባሰራጨው መረጃ አስታውቋል።
