አሜሪካ ለሃገራት የምትሰጠውን የገንዘብ ድጋፍ የማቆም እርምጃ እ.ኤ.አ. በ2030 ከ14 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ለሞት ሊዳርግ እንደሚችል ዘ ላንሴት የህክምና መጽሄት ላይ የወጣ ጥናት አመልክቷል።
ያለጊዜያቸው ለሞት ከሚዳረጉት ውስጥ አንድ ሶስተኛው ህጻናት መሆናቸውን ጥናቱ ያመላከተ ሲሆን፣ “ለብዙ ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ላላቸው ሃገሮች ይህ ክስተት ከዓለም አቀፍ ወረርሽኝ ወይም ከታላላቅ የትጥቅ ግጭት ጋር ሊወዳደር ይችላል” ጥናቱን ያዘጋጁት ዴቪድ ራሴላ ።
አክለውም “አሜሪካ የምታደርገው የገንዘብ ድጋፍ ለሁለት አስርት ዓመታት በጤና ላይ በተጋላጭ ህዝቦች መካከል ያለውን እድገት በድንገት የመቆም እንዲሁም ወደ ኋላ የመመለስ አደጋን ይቀንሳል” ሲሉ ገልጸዋል ።
ከ133 ሀገራት የተገኘው መረጃም እንደሚያሳየው የዩኤስኤአይዲ የገንዘብ ድጋፍ ከ2001 እስከ 2021 ባለው ጊዜ ውስጥ ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት የ91 ሚሊዮን ሰዎችን ከሞት መታደግ መቻሉን የጥናት ቡድኑ ገልጾል።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ በመጋቢት ወር የፕሬዚዳንት ትራምፕ አስተዳደር በዩኤስ ዓለም አቀፍ ልማት ኤጀንሲ ወይም ዩኤስኤአይዲ ከ 80% በላይ ፕሮግራሞችን መሰረዙን ማስታወቃቸው የሚትታወስ ነው።
