17 ተጠርጣሪዎች

Date:

የጀርመን ዐቃቤ ሕግ ቢሮ “ብርጌድ ንሓመዱ” የተባለ “ሽብርተኛ ቡድን” በመመሥረት እና አባል በመሆን በተጠረጠሩ ሰዎች ላይ ከፍተኛ አሰሳ መካሔዱን አስታወቀ። ብርጌድ ንሓመዱ
“የኤርትራ መንግሥትን ለመጣል ያለመ ዓለም አቀፍ ትሥሥር ያለው ኔትወርክ” እንደሆነ መቀመጫውን በካርልስሩኸ ያደረገው የጀርመን ዐቃቤ ሕግ ቢሮ አስታውቋል።

በ17 ተጠርጣሪዎች ላይ በስድስት የጀርመን ፌድራል ግዛቶች በሚገኙ 19 ቦታዎች አሰሳ የተካሔደው ትላንት ረቡዕ ነው። ተመሳሳይ አሰሳ በዴንማርክ ጭምር መካሔዱን የጀርመን ዐቃቤ ሕግ ቢሮ አስታውቋል።

በጀርመን በተካሔደው አሰሳ ከ200 በላይ የፖሊስ መኮንኖች ተሳትፈዋል። በመግለጫው መሠረት በቁጥጥር ሥር የዋለ ተጠርጣሪ የለም። አሰሳው ያነጣጠረባቸው ተጠርጣሪዎች “ብርጌድ ንሓመዱ” ውስጥ ከፍተኛ የአመራርነት ቦታ ያላቸው መሆናቸውን የምርመራ ውጤቶች እንደሚያሳዩ መሥሪያ ቤቱ አስታውቋል።

“ብርጌድ ንሓመዱ” በሔሰን ግዛት በምትገኘው ጊሰን ከተማ ዉስጥ በጎርጎሮሳዊው ነሐሴ 2022 እና መስከረም 2023 የኤርትራ የባሕል ፌስቲቫል ላይ የተቀሰቀሱ ኃይለኛ ኹከቶችን በማደራጀት ይወነጀላል። በመስከረም 2023 በሽቱትጋርት ከተማ በኤርትራውያን ማኅበር ስብሰባ ላይ ለተፈጠረ ኹከትም “ብርጌድ ንሓመዱ” ተጠያቂ ይደረጋል። በኹከቶቹ በርካታ የፖሊስ መኮንኖች መጎዳታቸውን የጀርመን ዐቃቤ ሕግ ቢሮ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

Dw

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግብጻዊቷ የቴሌቪዥን አዘጋጅ በዕፅ ዝውውር ወንጀል የሞት ፍርድ ተወሰነባት

የካይሮ የወንጀል ችሎት፤ ዕውቋን የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅ ሳራ ካሊፋን...

ከአሜሪካ ጋር የሚኖረው “የጨዋታው ሕግ ተቀይሯል፤ የተመጣጠነ ምላሽ ዘመን አብቅቷል

ኢራን ከአሜሪካ በኩል ለሚሰነዘርባት ጥቃት የምትሰጠው ተመጣጣኝ የአጸፋ ምላሽ...

የ2.5 ቢሊየን ብር ግዙፍ ፕሮጀክት በአታ ለማርያም ገዳም በመስከረም ወር የመሠረት ድንጋይ ሊያኖር ነዉ

​በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ የታዕካ ነገሥት...

የዲቪ ዕድለኞች የማመልከቻ ሂደታቸውን እንዲቀጥሉ ተወሰነ!

የአሜሪካ የፌዴራል ፍርድ ቤት በዲቪ ሎተሪ አመልካቾች የማመልከቻ ሂደት...