179 የገቢዎች አመራሮችና ባለሙያዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ

Date:

በአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ባለፉት 5 ወራት ለግብር ከፋዮች ተገቢው አገልግሎት ባለመስጠት ኃላፊነታቸው ባልተወጡ 179 አመራሮችና ባለሙያዎች ላይ የዲስፕሊን እርምጃ መወሰዱ ተገለፀ።

የቢሮው ሞደርናይዜሽን ዘርፍ በበጀት ዓመቱ 5ወራት ውስጥ በ179 ሰራተኞች ላይ የዲስፕሊን እርምጃ መወሰዱን ገልጿል ።

በቢሮው የሞደርናይዜሽን ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ መሀመድ አብዱራህማን በዕቅድ አፈፃፀም ውይይቱ በበጀት ዓመቱ የተሰሩ ስራዎች ፣ ያጋጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ መፍትሄዎች እንዲሁም የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ አስቀምጠዋል ።

አያይዘውም ከዋና መስራያ ቤት አንስቶ በሁሉም ቅርንጫፎች እና ወረዳዎች ጽህፈት ቤቶች ከሌብነትና ብልሹ አሰራር ፣ ከአገልግሎት አሰጣጥ ፣ ከስነ_ምግባር አኳያ ክትትልና ድጋፍ በሰርቪላንስ ካሜራ ፣ በምስለ ተገልጋይና በዕቅድ አፈፃፀም ዙሪያ ተደርጓልም ብለዋል ።

በዚህም ሃላፊነታቸው በአግባቡ ተወጥተው ባልተገኙ 20 አመራሮችና 159 ፈፃሚዎች ላይ የዲስፕሊን እርምጃ መወሰዱን ገልፀዋል ።

አክለውም በቀጣይ የክትትልና ድጋፍ ስራው የሚቀጥል መሆኑን ጠቁመው በአገልግሎት አሰጣጥ ፣ በሀርሞናይዜሽን ፣ በቲን ቁጥር አሰጣጥ ፣ በኢፋይልና ኢፔመንት ፣ በመዝጊያ ኪሊራንስ እንዲሁም በመማክርት ጉባኤን ውይይት የተጠናከረ ስራዎችን በመስራት ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት እንደሚገባ አሳስበዋል ።

የቢሮው ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አዳነ ሱሌ በበኩላቸው የሚሰጡ አገልግሎቶችን የጥራት ደረጃ በማሳደግ ገቢን በፍትሃዊነት መሰብሰብ ይገባል ብለዋል ።

አያይዘውም የከተማዋን የትኩረት ነጥቦችን የጋራ እውቀት በማድረግ አገልግሎት ጠያቂው ካለምንም እንግልት አገልግሎት የሚያገኝበትን ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር በየደረጃው ያለ አመራር ኃላፊነት መሆኑን አስገንዝበዋል ።
(አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ10 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ ጥቅምት 12 ቀን 2019...

ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ የፕላቲንየም ብራንድ የማስተር ካርድ ይፋ አደረጉ

ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ደንበኞች የፕሪሚየም...

የአሜሪካ የደህንነት ኃላፊ ኢራንን አስጠነቀቁ

ቡሔራዊ ደህንነት ዳይሬክተር ጄይ ክላይተን አርብ ዕለት ኢራን በውጭ...

ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ  በአመት ከ1.1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ታጣለች

85 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ በግብርናው ዘርፍ የተሰማራ ሲሆን...