የዩክሬን ፕሬዝዳንት ዘሌንስኪ ከትራምፕ ጋር ከተጋጩ በኋላ ለማዕድን ድርድር ‘ዝግጁ’ መሆናቸውን ተናገሩ

Date:

የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ከዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር በአደባባይ ቢጨቃጨቁም ከዋሽንግተን ጋር የማዕድን ስምምነት ለመፈራረም ዝግጁ ነን ብለዋል ። እሁድ እለት በለንደን ከአውሮጳ መሪዎች ጋር ከተካሄደው ወሳኝ የመሪዎች ጉባኤ በኋላ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ኪየቭ በስምምነቱ ለመቀጠል ዝግጁ መሆኗን ተናግረዋል፤ ይህም አርብ ዕለት ከትራምፕ ጋር ካደረጉት ግጭት በኃላ አነጋጋሪ አድርጎታል።

“ከዚህ ቀደም የተከሰቱት ሁኔታዎች ቢኖሩም መቀጠል የእኛ ፖሊሲ ነው። እኛ ገንቢዎች ነን። ለመፈረም ከተስማማን ዝግጁ ነን። እና እንደ እውነቱ ከሆነ፣ ዩናይትድ ስቴትስም ዝግጁ መሆኗን አምናለሁ፣” ሲሉ ዘለንስኪ በለንደን ስታንስተድ አውሮፕላን ማረፊያ ለጋዜጠኞች ቡድን በአስተርጓሚ ተናግረዋል። “ምናልባት አንዳንድ ነገሮችን ለመተንተን ጊዜ ያስፈልግ ይሆናል፣ ነገር ግን የዩክሬን አቋም እንዲሰማ ብቻ ነው የምፈልገው፤ የዩክሬን አቋም መሰማቱ ለእኔ በጣም አስፈላጊ ነው ሲሉ አክለዋል። ግንኙነታችን እንደሚቀጥል ይመስለኛል። ምክንያቱም ይህ ከግንኙነት በላይ ነው ሲሉ ተደምጠዋል።

በራችን ክፍት መሆን አለበት ፤ ዩክሬን በዓለም ላይ ትልቋ ሀገር አይደለችም ነገር ግን ሁሉም ሰው ለነፃነቱ እንዴት እንደሚታገል ማየት ይችላል ። “ያለምንም ጥርጥር ከዩናይትድ ስቴትስ የሚደረግልን እርዳታ እንደሚቀጥል እንተማመናለን” ሲሉ አክለዋል። “እንደዚህ አይነት እርዳታ ማቆም ፑቲንን ብቻ የሚረዳ ይመስለኛል። እናም በዚህ ምክንያት ዩናይትድ ስቴትስ እና የሠለጠኑ ዓለም ተወካዮች ብሎም የዚህ ዓለም መሪዎች በእርግጠኝነት ፑቲንን አይረዱም ብዬ አስባለሁ ሲሉ ተደምጠዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት በዛሬ ዕትሟ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ ነሔሴ 16 2018 ዓ.ም ገበያ...

ቱርክ ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ የእስር ማዘዣ አወጣች

ቱርክ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ ዓለም አቀፍ...

በመቀለ የሚካሄደው የአሸንዳ በዓል የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ተሰረዘ

በትግራይ በርካታ ታዳሚ በሚገኝበት በየዓመቱ የሚከበረው የአሸንዳ ባህላዊ በዓል...

የኢትዮጵያ ፖስታ 3 ሺሕ የሚጠጉ ቅርንጫፎቹን ወደ ባንክ ኤጀንትነት ለመቀየር እንቅስቃሴ ጀመረ

የኢትዮጵያ ፖስታ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ 3 ሺሕ በሚጠጉ ቅርንጫፎቹ...