19ኛው አዲስ ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል የመዝጊያ ስነ ሥርዓት ዛሬ ይካሄዳል

Date:

በየዓመቱ የሚካሄደው የአዲስ ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል የመዝጊያ ስነ ሥርዓት ዛሬ በጣልያን ካልቸር ኢንስቲቲዮት እደሚካሄድ ተገልጿል።

የመዝጊያ አምባሳደሮች፣የፊልም ባለሞያዎች፣የ ኢንሼቲቭ አፋሪካ ዋና ዳይሬክተር አቶ ክቡር ገና እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ይካሄዳል።

ለ አራት ቀናት ሲካሄድ የቆየዉ ፌስቲቫሉ ከግንቦት 13-ግንቦት 17 ድረስ በአራት የተለያዩ ማሳያ ቦታዎች ታይቷል።

የዘንድሮው ፌስቲቫል ለየት የሚያደርገው 28 የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑ ነው ሲሉ የ19ኛው አዲስ ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል ኮርዲኔተር መና ሀይሌ ገልፀዋል።

28ቱ ፊልሞች ከ 34 በላይ ሀገሮች የተሳተፉባቸው ሲሆን የተለያዩ የጣሊያን ፊልሞች እና ስድስት የኢትዮጵያ ፊልሞች ታይተዋል።

የመዝጊያ ፕሮግራሙ በጣሊያን ካልቸር ኢንስቲቲዩት እንደሚካሄድ እና መግቢያ በ ነፃ መሆኑን የ 19ኛው አዲስ ኢንተርናሽናል በፊልም ፌስቲቫል ኮርዲኔተር የሆኑት መና ሀይሌ ለግዮን መፅሄት ገልፀዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ፣ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አካልና የመንፈስ...

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ የአጼ ቴዎድሮስ የፀጉር ቁንዳል እና...

ፈረንሳይ የ54 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ለመስጠት ተስማምታለች

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የኃይል...

ትራምፕ ኢራን ላይ ያላቸው ትዕግሥት እየተሟጠጠ መሆኑን ተናገሩ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይናው መሪ ዢ ጂንፒንግ ጋር...