የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ የምስራች ግርማ የተወሰደው እርምጃ ንብረት ከመውረስ እስከ ተቋም ማሸግ መሆኑን ተናግረዋል።
ህገወጥ ንግድ ህጋዊ ነጋዴዎች ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ ከፍተኛ በመሆኑ አንስተው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በትኩረት እየሰራ በመሆኑ በ6 ወር ውስጥ 2 ሺህ 8 መቶ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን አስታውቀዋል ።
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከሚሰራው ስራ አንዱ ህገወጥ የጎዳና ንግድን መቆጣጠር መሆኑን አንስተው ከቀድሞ ጋር ሲነጻጸር መቀነሱን ተናግረዋል፡፡
የጎዳና ንግድ መቀነስ የተቻለው ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር በመቀናጀት በመስራት በሰንበት ገበያዎች እንዲሳተፉ በማድረግ በህጋዊ መንገድ የንግድ ስራ እንዲሰሩ ምቹ ሁኔታ በመፈጠሩ ነው ብለዋል።
አሐዱ ራድዮ
