Date:

ትራምፕ በአሜሪካ የሚኖሩ የ240 ሺ ዩክሬናውያንን ህጋዊ ፍቃድ ሊሰርዙ ነው

የትራምፕ አስተዳደር ከሩሲያ ጦርነት ሸሽተው የወጡ 240 ሺ ዩክሬናውያንን ጊዜያዊ ህጋዊ ፍቃድ ለመንጠቅ ማቀዱን ሮይተርስ የትራምፕ ከፍተኛ ባለስልጣንን እና ጉዳዩን የሚያውቁ ሶስት ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል። ሮይተርስ እንደዘገበው፣ ይህ ዩክሬናውያንን የማፈናቀል ሂደት በሚያዝያ ወር ላይ እንደሚጠበቅ እና ወደ በፍጥነት ተግባራዊ ሊያደረግ ይችላል ተብሏል።

እቅዱ ከፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ጋር ከፈጠሩት ፍጥጫ ቀደም ብሎ ነበር ተብሏል። በፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ስር ወደ አሜሪካ እንዲገቡ ወደ 1.8 ሚሊዮን ለሚጠጉ ስደተኞች የተዘረጋው ጥበቃን በመሰረዝ የትራምፕ አስተዳደር ሰፊ ስደተኞችን የማስወጣት ጥረት አካል ናቸው። ሆኖም ግን ከዋይት ሀውስ ምንም አይነት ይፋዊ ምላሽ አልተሰጠም።

የዩናይትድ ስቴትስ የሀገር ውስጥ ደህንነት ክፍል ቃል አቀባይ ትሪሲያ ማክላውሊን መምሪያው በአሁኑ ጊዜ ምንም አይነት መግለጫ አይሰጥም ብለዋል። የዋይት ሀውስ እና የዩክሬን ኤምባሲ አስተያየት እንዲሰጡ ለቀረበላቸው ጥያቄም ዝምታን መርጠዋል። በጃንዋሪ 20 የወጣው የትራምፕ ሥራ አስፈፃሚ ትዕዛዝ መሰረት በአሜሪካ ለመቆየት ፍቃድ ያጡ ስደተኞች የተፋጠነ የመባረር ሂደቶች ሊገጥማቸው ይችላል::

ቀዳሚ ጽሑፍ
ቀጣይ ጥሑፍ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...