Date:

የሶፍ ዑመር የባቡር መንገድ ግንባታ በተያዘው ዓመት ይጠናቀቃል

በሶፍ ዑመር ዋሻና ሎጅ ፕሮጀክቶች ውስጥ ለቱሪስት አገልግሎት መስጫ እየተገነባ የሚገኘው የባቡር መስመር በተያዘው ዓመት እንደሚጠናቀቅ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የባቡር ዘርፍ ምክትል ስራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ስለሺ ካሳ እንደገለጹት፤ የባሌ አካባቢን ቱሪዝም ለማሳደግ ሶፍ ዑመር ላይ እየተገነባ ያለው የባቡር መንገድ ግንባታ በዚህ ዓመት ይጠናቀቃል።

ኢትዮጵያ ከአሏት ዕምቅ ሀብቶች መካከል አንዱ ቱሪዝም ነው ያሉት ኢንጂነር ስለሺ፤ ሀገሪቱን ባላት የቱሪዝም ሀብት ልክ ተጠቃሚ ለማድረግ በትራንስፖርት ማስተሳሰር ቀዳሚ አጀንዳ መሆኑን ጠቁመዋል።

በውስጥ አቅም በመገንባት የመጀመሪያ የሆነው ይህ ፕሮጀክት እስካሁን ከ50 በመቶ በላይ መጠናቀቁን ገልጸው፣ አጠቃላይ ርዝመቱ አምስት ኪሎ ሜትር መሆኑን አስረድተዋል።

የባቡር መንገዱ በቀጣይም እንደ ሁኔታው ሊሰፋ የሚችልበት ዕድል መኖሩን ጠቅሰው፤ ለጎብኝዎች ያለ ስጋት መንቀሳቀስ የሚያስችል መሆኑን አብራርተዋል።

በሀገሪቱ በአጠቃላይ የባቡር መስመሮች ላይ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን የጠቀሱት ኢንጂነር ስለሺ፤ አዋሽ – ኮምቦልቻ – ሀራ ገበያ የባቡር መንገድ ከዚህ በፊት የነበረውን የመሠረተ ልማት ስርቆት ችግር በመቅረፍ ከአማራና ከአፋር ክልሎች ጋር በተሰራ ስራ መቀነስ መቻሉን አያይዘው አመልክተዋል።

የባቡር መስመሩ አገልግሎቱን ለማስጀመር በውስጥ አቅም የመጠገን ተግባራት እየተከናወኑ ሲሆን፤ በቅርቡም ወደ ስራ ለማስገባት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

ጋዜጣ ፕላስ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተፈናቀሉ ዜጎች በተጠለሉበት አካባቢ በቋሚነት መኖር የሚያስችላቸው 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ ከበኦሞ...

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...