233 ቢሊየን ብር መሰብሰብ ተችሏል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Date:

በ2017 የበጀት ዓመት 241.4 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ የነበረ ሲሆን፣ 233 ቢሊየን ብር በመሰብሰብ የዕቅዱን 96.5 በመቶ ማሳካት መቻሉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ ይህም ከባለፈው በጀት ዓመት 83.3 ቢሊየን ብር ብልጫ ወይም 45 በመቶ እድገት በከተማዋ ገቢ ላይ ያሳየ ነው ብለዋል።

ያልተሰበሰበው 8 ቢሊየን ብር ከእርዳታ እና ብድር ይገኛል ተብሎ በተጨማሪ በጀት የታወጀ እንደነበርም አንስተዋል።

“ለውጥና እድገት በራስ አቅም ሲሆን መሰረቱ ሰፊ፤ ምሰሶውም ጠንካራ ይሆናል” ያሉት ከንቲባዋ፣ ለተገኘዉ ስኬት የከተማዋን ነዋሪዎች፣ ግብር ከፋዮችን፣ የገቢዎች ቢሮ ሰራተኞችና አመራሮችን እንዲሁም ባለድርሻ አካላትን አመስግነዋል።

“ነገም አቅማችን እናንተዉ ናችሁና ፤ ችግሮችን እያረምን በራስ አቅም፣ በትብብር፣ በጠንካራ እምነት እና የስራ ባህል የመራናት ከተማችን እድገት ይቀጥላልም ነው ያሉት።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...