24 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ግዥ መፈፀሙን ግብርና ሚኒስተር አስታወቀ

Date:

24 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ግዢ ተፈፅሞ ወደ ሃገር ውስጥ የማጎጎዝ ስራ አየተሰራ መሆኑን ግብርና ሚኒስተር አስታውቋል

እስካሁን ባለው አፈፃፃም 8 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሃገር ውስጥ ተጎጉዞ መአከላዊ መጋዘን መድረሱን የግብርና ሚኒስተር የህዝብ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ከበደ ላቀው ላቀው ለጣቢያችን ተናግረዋል ::

መንግሥት ድጎማ ከሚያደርግባቸው ግብአቶች አንዱ የአፈር ማዳበሪያ መሆኑን የገለፁት የህዝብ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚዉ 84 ቢሊዮን ብር ለአፈር ማዳበሪያ ድጎማ መደረጉን አስታዉቀዋል ፡፡

የአፈር ማዳበሪያን ከዉጭ የማጎጎዝ ሂደቱ በታቀደዉ ልክ እየሄደ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ከበደ ወደ ሃገር ዉስጥ የማስገባቱ ሂደት እስከ ሀምሌ ወር ድረስ እንደሚቀጥል ገልፀዋል ፡፡

የግብርና ሚኒስቴር ለእያንዳንዱ ክልል የሚደርሰዉን የአፈር ማዳበሪያ በመተንተን ተደራሺ እንዲሆን እየሰራ እንደሆነም ተጠቁሞል ፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነ ኢየሱስ በጡረታ ከኃላፊነታቸው ተሰናበቱ

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያንና የአዲስ አበባ አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ...

አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ አዲስ መግለጫ አወጣች

ታዋቂዋ አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ ለስፖርት ወዳጆችና ለደጋፊዎቿ ወቅታዊ መረጃ...

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...