37ኛው የዓለም አቀፉ የሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ስብሰባ በአዲስ አበባ ይካሄዳል

Date:

የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴረሽን ኢሠማኮ በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄደውን 37ኛውን የዓለም አቀፉ የሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ስብሰባ በአዲስ አበባ እንደሚያካሂድ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

በተጨማሪም ኢሠማኮ በቀጣይ ቀናት የመላው ቻይና የሠራተኛ ማኅበራት የሥራ ጉብኝትን ጨምሮ የአፍሪካ ቀንድ ሠራተኛ ማኅበራት ስብሰባዎችን በመዲናዋ እንደሚያካሂድ ይፋ አድርጎል።

37ኛው ስብሰባ ከህዳር 23 እስከ 25 2018 ዓ.ም ለሶስት ቀናት የሚካሄድ መሆኑን የኢሠማኮ ምክትል ፕሬዝደንት አቶ ድሪብሳ ለገሰ ተናግረዋል።

ይህ ጉባኤ በአዲስ አበባ እንዲካሄድ ምክንያት የሆነው ኢሠማኮ ከዓለም አቀፍ የሠራተኛ ማኅበራት ጋር ያለው የሥራ ግንኙነት ተቀባይነት ያለው በመሆኑ ነው ሲሉ አቶ ድሪብሳ ገልፀዋል።

በስብሰባው ከመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ የሠራተኛ ማኅበራት ተወካዮችን ጨምሮ ከ150 በላይ ተፃታፊዎች ከተለያዩ ሀገራት እንደሚገኙ አራዳ ኤፍ ኤም ሰምቷል።

በተጨማሪም የቻይና ቤጂንግ ሰራተኛ ማህበራት ጎብኝት እንደሚያደርጉ የተገለፀ ሲሆን በማህበራቱ መካከል ያለውን መልካም የሥራ ግንኙነት ለማጠነከር ያሰበ ስለመሆኑን ኢሠማኮ ገልፆል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...

አገር እንዲህ ዓይንህን ለአፈር ይባላል?

በተጀመረው የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ መሸነፏን ተከትሎ አፍሪካ...

አሜሪካ እና ኢራን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በ24 ሰዓት ውስጥ እንደሚፈራረሙ ፓኪስታን አስታወቀች

ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በሰላም ድርድሩ ማዕቀፎች ላይ መስማማታቸውን...