“ቅን” የተሠኘው የድምፃዊ የግጥምና ዜማ ደራሲ አቤል ሙሉጌታ 4ተኛ የሙዚቃ አልበም ዛሬ ከሰአት በድምፃዊው የዩቱብ ቻናል ላይ ይለቀቃል
ይህ በርካታ የሀገራችን የሙዚቃ ባለሙያዎችን ያሳተፈውና የሀገራዊ፣የማህበራዊ፣የፍቅር፣የፍልስፍናና ታሪካዊ ጉዳዮችን የሚያነሳው የሙዚቃ አልበም በዛሬው እለት ለአድማጮች በራሱ የአቤል ሙሉጌታ የዩቲዩብ ቻናል ይለቀቃል።
የድምፃዊ የግጥምና ዜማ ደራሲ አቤል ሙሉጌታ 4ተኛ አልበም 14 ትራኮችን የያዘ ሲሆን ስራውን ሰርቶ ለማጠናቀቅም 5 ዓመታትን መውሰዱ ተነግሯል፡፡
የሁሉም ትራኮች ግጥምና ዜማ በራሱ በድምፃዊው በአቤል ሙሉጌታ ሲሰሩ በቅንብር ካሙዙ ካሳ፣አቤል ጳውሎስ፣ታምሩ አማረ፣አዲስ ፍቃዱ፣ሮቤል እንዳለ፣አብርሃም ኪዳኔና ሙሳ ማቲ በሚክሲንግ ሰለምን ሃ/ማርያም፣አቤል ጳውሎስና አብርሃም ኪዳኔ በማስተሪንግ ኪሩቤል ተስፋዬ ተሳትፈውበታል፡፡
በኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንደስትሪ ውስጥ በርካታ ስራዎችን በመስራት ከ90ዎቹ መጨረሻ አንስቶ እጅግ ተወዳጅነትና ተቀባይነትን ያገኘው ድምፃዊ የግጥምና ዜማ ደራሲ አቤል ሙሉጌታ 4ተኛ አልበሙን ለማውጣት ዝግጅቱን ሙሉ በሙሉ አጠናቋል።
በዛሬው እለት አቤል ሙሉጌታ በተሰኘው የዩቱብ ቻናሉ ለአድማጮቹ የሚያደርስ ሲሆን በ1999 “አላማሽም” በ2003 “ተገርሜ” በ2011 “እንነጋገር” በተሰኙት የሙዚቃ አልበሞቹ በህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅነትና ተቀባይነት ያገኘው ድምፃዊ አቤል ሙሉጌታ ለበርካታ የሀገራችን አንጋፋና ወጣት ድምፃዊያን ማለትም ፀሃዬ ዮሃንስ፣ዳዊት ፅጌ፣ብዙአየሁ ደምሴ፣ሄለን በርሄ፤ቬሮኒካ አዳነ፣ራሄል ጌቱ፣ተመስገን ገ/እግዚአብሔር፣መስፍን(ነይ በክረምት)ን ጨምሮ ለሌሎች በርካታ ድምፃውያን ተወዳጅ የሆኑ የግጥምና ዜማ ስራዎችን ሰርቷል፡፡
