53 ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው መመለሳቸው ተገለጸ

Date:

መንግሥት በማይናማር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ እና ታይላንድ ወታደራዊ ካምፕ ተጠልለው የነበሩ 53 ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ማድረጉን አስታወቀ።

መጋቢት 7 ቀን 2017 ዓ.ም 23 ዜጎችን እንዲሁም መጋቢት 8 ቀን 2017 አ.ም ደግሞ 30 ዜጎችን በአጠቃላይ በካምፑ የነበሩትን 53 ዜጎች እንዲመለሱ ማድረግ መቻሉን ገልጿል።

ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ የተደረጉት ኢትዮጵያውያኑ ከማይናማር እገታ ወጥተው ታይላንድ ወታደራዊ ካምፕ የነበሩ መሆናቸውን ጠቁሟለ።

ኢትዮጵያውያኑ ወደ ሀገራቸው እነዲመለሱ የተደረገው ከኢትዮዽያ አየር መንገድ ጋር በመተባበር እና በአካባቢው ከሚገኙ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመነጋገር መሆኑን አስታውቋል።

እስካሁን ከማይናማር እገታ ወጥተው ታይላንድ ወታደራዊ ካምፕ የነበሩ በመጀመሪያውና ሁለተኛው ዙር በጠቅላላው 130 ዜጎችን ወደ ሀገራቸው መመለስ መቻሉን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኮሪያ ዘማቾች ያስመዘገቡት አኩሪ ታሪክ በዓለም ሲታወስ ይኖራል

75ኛ ዓመት የኮሪያ ዘማቾች መታሰቢያ በዓል አዲስ አበባ በሚገኘው...

አሜሪካ በጣለችው የባህር ላይ እገዳ ሳቢያ ኢራን 4.8 ቢሊዮን ዶላር አጣች

በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትዕዛዝ በኦማን ባህረ ሰላጤ ላይ...

ኢሕአፓ ሊያካሂድ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ ማራዘሙን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ሚያዚያ 30 ቀን 2018...

እሁድ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ ይደረጋሉ

መነሻውንና መድረሻውን መስቀል አደባባይ የሚያደረገው ዓለም አቀፉ የዛይድ የበጎ...