6ኛው የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታ በጅማ ከተማ ይካሄዳል

Date:

ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ከሰኔ 10 እስከ ሰኔ 19 ቀን 2017 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል ጅማ ከተማ የሚያካሂደው 6ኛው የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታ ቅድመ ዝግጅት ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁን የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ መክዩ መሐመድ አስታወቁ።

ሚኒስትር ዴኤታው ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ጨዋታው ሀገራዊ አንድነትን ከማጠናከር ባሻገር፣ ለኦሎምፒክ ተተኪ ስፖርተኞችን የማፍራት ዓላማ እንዳለው ገልጸዋል።

አቶ መክዩ መንግሥት ለስፖርት ዘርፍ ከፍተኛ ትኩረት መስጠቱን ጠቁመው፣ በርካታ የስፖርት መሠረተ ልማቶችን ከመገንባት ባለፈ፣ በዘርፉ ያጋጠሙ ችግሮችን በመለየት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

ለረጅም ጊዜ ተቋርጠው የቆዩ ስፖርታዊ ውድድሮች በመንግሥት ቁርጠኝነት በአዲስ መልክ እየተካሄዱ መሆኑንም አውስተዋል።

6ኛው የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታ ከውድድር ባሻገር፣ ማኅበራዊ ትርክቶችንና እሴቶችን ለማኅበረሰቡ የሚያሰርጽበት መድረክ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው አስረድተዋል።

በመግለጫቸውም በስፖርት ዘርፍ የሚታዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት የሕግ ማዕቀፎችን ማሻሻል አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል።

የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ማኅበራዊ አብሮነት የሚጠናከርበትና ስፖርታዊ ጨዋነት የሚሰፍንበት እንዲሆን ታስቦ መከናወናቸው ተገልጿል።

በጨዋታው ሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የሚሳተፉ ሲሆን፣ ውድድሩ በ26 የስፖርት ዓይነቶች ይካሄዳል።

ጨዋታው አገራቸውን በኦሎምፒክ የሚወክሉ ተተኪ ስፖርተኞችን ማፍራት ዓላማው ሲሆን፣ በተለይ ከቀበሌ ጀምሮ ያሉ አዳዲስ የውድድር መድረክ ያላገኙ አትሌቶች የሚሳተፉበት መሆኑ ልዩ ያደርገዋል።

መንግሥት በቂ ዝግጅት ባደረገበት በዚህ ጨዋታ፣ ከውድድሩ ጎን ለጎን በርካታ ዝግጅቶች እንደሚኖሩ ተገልጿል።

ከእነዚህም መካከል፡-

ሀገራዊ አንድነትን የሚያጠናክር የፓናል ውይይት
የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ፣ የልማት ሥራዎች ጉብኝት
ማኅበረሰብ አቀፍ የአካል ብቃት ስፖርታዊ እንቅስቃሴ
ይገኙበታል።

በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አዘጋጅነትና በስፖርት ፌዴሬሽኖች የሚመራው 6ኛው የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታ የኦሎምፒክ መርህን በመከተል የችቦ ቅብብሎሽ መርሃ ግብር እንደሚካሄድም በመግለጫው ተጠቁሟል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ሴቶችን በቤት ውስጥ በማገዝ  መልካም ማህበረሰብ መፍጠር ተጀምሯል

በቤት ውስጥ የሚሠሩ ተግባራትን ተከፋፍሎ በመሥራት ሴቶችና እናቶችን መደገፍ...

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ፣ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አካልና የመንፈስ...

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ የአጼ ቴዎድሮስ የፀጉር ቁንዳል እና...

ፈረንሳይ የ54 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ለመስጠት ተስማምታለች

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የኃይል...