6 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ የጫኑ መርከቦች የሆርሙዝ ወሽመጥን አቋረጡ

Date:



ለሁለት ወራት በባሕረ ሰላጤው አገራት ቆመው የነበሩ ሦስት ግዙፍ ነዳጅ ጫኝ መርከቦችረቡዕ ዕለት የሆርሙዝ ወሽመጥን ማቋረጣቸው ተገለጸ።ከ

መካከለኛው ምሥራቅ ወደ ቻይና እና ደቡብ ኮሪያ የሚጓጓዝ 6 ሚሊዮን በርሜል ድፍድፍነዳጅ የጫኑ ናቸው የተባሉት እነዚህ መርከቦች ወደ እስያ ጉዞ መጀመራቸውን ኤልኤስኢጂ እና ኬፕለር የተባሉ የመርከብ እንቅስቃሴንየሚከታተሉ ተቋማት አስታውቀዋል።እነዚ

ህ ግዙፍ ነዳጅ ጫኝ መርከቦች በዚህ ወር ኢራን እንዲያልፉ ከፈቀደችላቸው እናባሕረ ሰላጤውን ለቅቀው ከወጡ በጣት የሚቆጠሩ መርከቦች መካከል መሆናቸው ተገልጿል።የካቲት

21 2018 ዓ.ም. እስራኤል እና አሜሪካ በቴህራን ላይ ጦርነት ከከፈቱበኋላ የዓለም አንድ አምስተኛ ነዳጅ የሚተላለፍበት ሆርሙዝ በመዘጋቱ ከፍተኛ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ተከስቷል።የደቡብ

ኮሪያን ባንዲራ የሚያውለበልበው እና 2 ሚሊዮን በርሜል የኩዌት ድፍድፍ ነዳጅንየጫነው ግዙፍ መርከብ ሁለት የቻይና መርከቦችን ተከትሎ ወሽመጡን ረቡዕ ዕለት አቋርጧል።የኬፕለር

መረጃ እንደሚያሳየው መርከቡ ጭነቱን ለማራገፍ የአገሪቱ የነዳጅ ማጣሪያወደሚገኝበት ኡስላን እያመራ ነው።የደቡብ ኮሪ

ያ ኤነርጂ ኩባንያ ኤስኬ ኢነርጂ በጉዳዩ ላይ መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛሳይሆን ቀርቷል።

BBC

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ቱርክ ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ የእስር ማዘዣ አወጣች

ቱርክ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ ዓለም አቀፍ...

በመቀለ የሚካሄደው የአሸንዳ በዓል የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ተሰረዘ

በትግራይ በርካታ ታዳሚ በሚገኝበት በየዓመቱ የሚከበረው የአሸንዳ ባህላዊ በዓል...

የኢትዮጵያ ፖስታ 3 ሺሕ የሚጠጉ ቅርንጫፎቹን ወደ ባንክ ኤጀንትነት ለመቀየር እንቅስቃሴ ጀመረ

የኢትዮጵያ ፖስታ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ 3 ሺሕ በሚጠጉ ቅርንጫፎቹ...

«ግብጽ ዛቻውን አቁማ ወደ ድርድር ትግባ!»

ታዋቂው የአፍሪካ ፖለቲካ ተንታኝ ዶ/ር ዴቪድ ማትሳንጋ ግብጽ በኢትዮጵያ...