905 የጥሪ ማዕከል አገልግሎት ሀገር አቀፍ የደንበኞች ጥሪን  ሊያስተናግድ ነው

Date:

የኢትዮጵያ  ኤሌክትሪክ አገልግሎት በአዲስ አበባ ብቻ ተወስኖ የቆየውን 905 አጭር  ሥልክ ቁጥር የጥሪ ማዕከል አገልግሎት ወደ ሀገር አቀፍ ደረጃ ሊያሳድግ ነው።

አዲስ አበባ ላይ ብቻ ተወሰኖ  የነበረው  የደንበኞች የጥሪ ማዕከል አገልግሎት ከ2018 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ጀምሮ ሀገር አቀፍ ሊደረግ ነው።

የአገልግሎቱ የደንበኞች ግንኙነት ማዕከል ኃላፊ ስምረት በለጠ  እንደተናገሩት፤ የደንበኞችን ጥሪ የመቀበል አቅም በማሳደግ የጥሪ ማዕከል አገልግሎት ሀገር አቀፍ ለማድረግ  የሚያስችል አሰራር ተዘርግቷል።

ቀደም ሲል የጥሪ ማዕከሉ 905 በመባል ለአዲስ አበባ ከተማ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ደንበኞች ብቻ  የጥሪ አገልግሎት ይሰጥ እንደነበር ጠቅሰው፤ ተቋሙ በ2017 በጀት ዓመት ባደረገው ሪፎርም የደንበኞች አገልግሎት ማዕከል በአዲስ መልኩ እንዲደራጅ መደረጉን ጠቁመዋል፡፡

Gazette_Plus

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 1 2018 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!

በኢትዮጵያ ነፃ ኘሬስ ከ25 ዓመት በላይአገልግለናል !!! -የአርበኞች አደራና የትውልዱ...

ከሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የተላለፈ ጥሪ

በክልላችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደገ የመጣው የተሳሳተ ስሌት የወለደው...

በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ በከባድ መሳሪያዎች የታገዘ  የተኩስ ልውውጥ ተካሄደ

ለዓለም የንግድ ሰንሰለት እጅግ ስትራቴጂካዊ በሆነው የሆርሙዝ ባህረ ወሽመጥ...

የሲ.ኤን.ኤን መስራች ቴድ ተርነር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የዓለማችን ግዙፍ የዜና አውታር ሲኤንኤን መስራች ቴድ ተርነር በ87...