በደራሲ ንጉሤ አየለ ተካ የተፃፈው፣ ከፍተኛ ምርምር የተደረገበት “ኦዛና ምኒልክ” የተሰኘ ድንቅ መፅሐፍ የፊታችን ቅዳሜ ሰኔ 28 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰዓት በወመዘክር አዳራሽ ይመረቃል፡፡
ከዚህ ቀደም “ታላቁ ጥቁር” የተሰኘውን ከፍተኛ ተነባቢነትን ያገኘ በዳግማዊ ምኒልክ ዙሪያ ላይ ያተኰረ መፅሐፍ አሳትሞ ለንባብ ያቀረበው ንጉሤ አየለ አሁን ደግሞ ከፍተኛ ምርምር በማድረግ “ኦዛና ምኒልክን” ለንባብ አብቅቷል፡፡
“ኦዛና ምኒልክ” ስለ ዳግማዊ ምኒልክ ያልተነገሩ ዕውነታዎችን በዝርዝር የሚያስረዳ ጥልቅ የምርምር ሥራ ሲሆን 460 ገፆችንም ይዟል፡፡
ደራሲ ንጉሤ አየለ ተካ ፣በታላላቅ ቤተ መፅሐፍት ውስጥ ጊዜውን በማሳለፍ አዳዲስ የታሪክ ዕውነቶችን ለመጀመሪያ ጊዜ ለአንባቢ ፅፎ ያቀረበ ሲሆን መኖሪያውንም በአሜሪካን አገር ያደረገ ነው።
ንጉሤ አየለ ተካ፣ ከዚህ ቀደም ሐኖስ ፣የገራዶ ዋሽንት፣ ጣዝማ እና ሌሎች 7 መፅሐፍትን ለንባብ ያበቃ ሲሆን በ1970ዎቹ አጋማሽ ከኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነ- ፅሑፍ ክፍልም የተመረቀ ነው፡፡
የምረቃ መርሐ- ግብሩ ላይ የሥነ ፅሑፍ ወዳጆች፣የደራሲው አድናቂዎች እና ሌሎች እንግዶችም እንደሚታደሙ ይጠበቃል፡፡
የመፅሐፍ ምረቃ ሁነት ዝግጅቱ በተወዳጅ ሚድያና ኰምዩኒኬሽን የተሰናዳ ሲሆን መድረክ መሪውም ዕዝራ እጅጉ ነው።
