በባህልና በልማት ሥራቸው የሚታወቁት ደራሲ ገብረኢየሱስ የአጋዝነት ማዕረግ ተሰጣቸው

Date:

በቋንቋ፣ በባህልና በማኅበረሰብ ልማት ዘርፎች ያበረከቷቸው የህይወት ዘመን አገልግሎቶች “አጋዝ” እንዳስባላቸው የባህላዊ ስም ስያሜ የሰጧቸው ሽማግሌዎች ተናግሯል፡፡

አጋዝ ከመባላቸው አስቀድሞ ግን የማዕረጉ ተገቢነት ላይ በየጆካ ሽማግሌዎች ጭምር ምክክር ተደርጎበት መፅደቁንም አስታውሰዋል፡፡

በጉራግኛ፣ አማርኛ እና እንግሊዝኛ 16 መጽሐፍትን የጻፉትና ለጉራጌ ባህልና ቋንቋ ልማት እንዲሁም ጉርሐልድን በመመስረትና በማገልገል ለነበራቸው የሕይወት ዘመን አገልግሎት የምስጋና መርኃግብር በተዘጋጀላቸው ዕለት ነው “አጋዝ” የተባሉት፡፡

ከማዕረግ ስያሜው ጋር የጉራጌ አባቶች ባሕላዊ ዘንግ (እንጣር)፣ ባርኔጣ፣ ቡልኮና ጭራ (ወስመጫ) ተበርክቶላቸዋል፡፡

የጉራጌ ዞን አስተዳደሪ ተወካይና አማካሪ አቶ ዳርጌ ተክሌ ዞኑ ላበረከቱት ሁሉ እንደሚያመሰግን የሚገልፅ የምስክር ወረቀት አበርክተውላቸዋል፡፡ በሕይወት ዘመናቸው ለማኅበረሰቡ ያበረከቱት አስተዋፅዖ ከፍተኛ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

በዕለቱ ከረዥም ዓመታ በኋላ ለኹለተኛ ጊዜ የታተሙት የጫሙት ሽካ እና ተኬትነት አጂነት (አገኪ) ዳግም ታትመው ተመርቀዋል፡፡

ብርጋዴር ጄነራል ተስፋዬ ኃ/ማርያምን ጨምሮ በዕለቱ የተገኙት እንግዶች መጽሐፎቹን የመረቁ ሲሆን ኹለቱንም መጽሐፍት በክብሩ መጽሐፍት መደብርና በሓሪ ዲጂታል በኩል ማግኘት ይቻላል፡፡

የዝግጅቱ ፎቶው  በሓሪ ቴሌግራም ቻናል ላይ ታገኙታላችሁ!

የአጋዝ ገብረኢየሱስ ኃ/ማርያም የምስጋና ዝግጅት በደመቀ መልኩ መጠናቀቁን የገለፁት አዘጋጆቹ ለተሳታፊዎች ምስጋና አቅርበዋል፡፡

@Haridigetal

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...