የዩኒሴፍ ሃላፊ ካትሪን ሩሴል እያንዳንዱ ደቂቃ ሕይወታቸውን ለማዳን ጥቅም አለዉ ሲሉ ገልጸዋል፡፡
የተባበሩት መንግስታት የህጻናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) ሃላፊ ካትሪን ሩሴል፤ በጋዛ የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት በጣም የተገደበ በመሆኑ ጨቅላ ህጻናት ለተመጣጠነ ምግብ ዕጥረት ተጋልጠዋል ብለዋል፡፡
በኤክስ ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልዕክት በጋዛ በሺዎች የሚቆጠሩ ሕፃናት የእርዳታ አቅርቦት በጣም እየተስተጓጎለ በመሆኑ የተመጣጠነ ምግብ ማግኘት አልቻሉም ሲሉ ገልጸዋል፡፡
የእስራኤል ቀጣይነት ያለው ጥቃት በሴቶች እና ህጻናት ላይ እያደረሰ ያለውን ተጽዕኖ የገለጹት ሃላፊዋ፤ ብዙ እናቶች ተገድለዋል ወይም የተመጣጠነ ምግብ ዕጥረት ስላጋጠማቸዉ ልጆቻቸዉን ጡት ማጥባት ባለመቻላቸዉ ለሞት ወይም ለዘላቂ የጤና ጉዳት ተጋልጠዋል ብለዋል፡፡
ዓለም አቀፍ የተኩስ አቁም ጥሪ ቢደረግም እስራኤል ከጥቅምት 2023 ጀምሮ ከ57 ሺህ የሚበልጡ ፍልስጤማውያንን ህይወት ቀጥፋለች ተብሏል፡፡
የዓለም ዓቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ባለፈው ህዳር ኔታንያሁ እና የቀድሞ የመከላከያ ሚኒስትሩ ዮአቭ ጋላንት በጋዛ የጦር እና በሰብአዊነት ላይ በፈጸሙት ወንጀሎች ላይ የእስር ማዘዣ ማዉጣቱ ይታወሳል ሲል የዘገበዉ አናዶሉ ነዉ፡፡
