የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት 163 ቢሊየን ብር ገቢ ሰበሰበ፡፡
የቢሮው ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዳሉት÷ በበጀት ዓመቱ የከተማዋን የገቢ አማራጮች በአግባቡ በመጠቀም ረገድ አመርቂ ውጤት ተመዝግቧል፡፡
በዚህም በዓመቱ መጨረሻ 156 ቢሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ 163 ቢሊየን ብር መሰብሰበ መቻሉን ነው የተናገሩት፡፡
ገቢው ከቀጥታ ታክስ፣ ቀጥተኛ ካልሆነ ታክስ፣ ከማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት እና ከሌሎች መሰብሰቡን አስረድተዋል።
በቀጣይ የከተማዋ ኢኮኖሚ ማመንጨት በሚችለው ልክ ገቢ ለመሰብሰብ የተለያዩ አሰራሮችንና ቴክኖሎጂዎችን ለመተግበር ዝግጅት ተደርጓል ነው ያሉት፡፡
በተለይም በግብር አሰባሰብ ሒደት ላይ የሚነሱ ቅሬታዎችን መፍታት የሚያስችሉ 24 አዳዲስ አሰራሮችን ወደ ሥራ ለማስገባት በትኩረት ይሰራል ብለዋል፡፡
