ያለ ኢንተርኔት የሚሰራው መልዕክት መላላኪያ

Date:

የቴክኖሎጂው ዓለም ሰዎች ያለ ኢንተርኔት የሚሰራ አዲስ የመልዕክት መላላኪያ መተግባሪያ ይፋ አድርገዋል።

ስልክን በብሉቲዝ በማገናኘት ብቻ የሚሰራው ይህ መተግበሪያ ቢት ቻት (Bit Chat) የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን፥ ከኤክስ መስራቾች አንዱ በሆነውና የብሎክ ቴክኖሎጂና ፋይናንስ ኩባንያ መስራች ጃክ ዶርሲ አማካኝነት ወደ ስራ የገባ ነው።

መተግበሪያው ኢንተርኔት በሌለበት ወቅትም ምንም አይነት የኢሚል አድራሻ ወይም የስልክ ቁጥር ሳይጠይቅ ወደ ተገልጋዩ የስልክ ቀፎ መልዕክቶችን መለዋወጥ የሚያስችል መሆኑ ነው የተገለጸው።

በአብዛኛው ግላዊ ይዘት የተላበሰና ሚስጥራዊነቱም የተጠበቀ ሲሆን፥ ለተገልጋዮች አዲስና ምቹ ነው ተብሏል።

አዲሱ መልዕክት መላላኪያ ከዚህ ቀደም ከተዋወቁት አንጻር በአቀራረቡ ቀለል ያለ መሆኑ በቀላሉ የተገልጋዮችን ትኩረት እንዲስብ ያስችለዋልም ነው የተባለው።

እንደ ኋትስአፕ፣ ሜሴንጀር እና ቴሌግራም ሞባይል ዳታ ወይም ዋይፋይ ሳያስፈልገውና ስልክዎን በኦፍላይን ሞድ አድርገውትም መስራቱ ተመራጭነቱን ከፍ እንደሚያደርገው ታምኖበታል።

ተጠቃሚዎቹ ብሉቱዝ ብቻ በማገናኘት ማንኛውንም አይነት ሜሴጅ የሚላላኩበት ይህ መተግበሪያ አሁን ላይ ወደ ስራ ገብቷል።

ለአይፎን ተጠቃሚዎች እየሰራ ሲሆን በቅርቡም በአንድሮይድ ስልኮች download bitchat apk . ይጀመራል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ካናዳ ምዝገባም ሆነ ስምሪት አልተጀመረም

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መቀመጫውን ካናዳ ካደረገው "ፊውቸር ፊት ኢንተርናሽናል"...

የክቡር ዶክተር ጋሽ መሐሙድ አዲስ አልበም ለአድማጮች ሊደርስ ነዉ

ታዋቂው ድምፃዊ ክቡር ዶክተር አርቲስት መሐሙድ አሕመድ «ለታሪክ» የተሰኘውንና...

ሜታ ‘ፌስቡክ እና ኢንስታግራም በቀረበባቸው ክስ 18 ቢሊዮን ዶላር ለመክፈል ተስማማ

ግዙፉ የማኅበራዊ ሚዲያ ኩባንያ ሜታ በፌስቡክ እና በኢንስታግራም ምክንያት...