የሥዕል ሥራዬ አገሬን በዓለም መድረክ እንዳስተዋውቅ ረድቶኛል

Date:


ሥዕል ያለፉ ታሪኮች፣ ባህል፣ አሁናዊ  አኗኗር፣ ቋንቋን ስነ-ጥበባዊ በሆነ መንገድ የመግለጽ አቅም እንዲሁም ወደፊት ሊሆን ይችላል ተብሎ የሚታሰብን ሁነት በመተንበይ የማሳየት አቅም አለው።

በርካቶችም በስዕል ሥራዎቸው የአገራቸውን ውበት ለጥበብ አፍቃሪያኑ አስተዋውቀዋል።

ሠዓሊ እያሱ ሲሳይ፤ በተሰጠኝን መክሊ የተለያዩ ስዕሎችን በማዘጋጀት አገሬን በዓለም መድረክ ለማስተዋወቅ ችያለሁ ሲል ይገልጻል።

“ሥዕልን የምስለው የነበሩ ታሪኮቻችንን፣ ውበት፣ ባህል፣ ቋንቋ፣ የሀገር ገፅታ መልከዓ-ምድር ውበት እና ሳቢነትን በመጨመር ሰዎች ሲያዩት መንፈሳቸው የሚታደስበት ሁኔታ ለመፍጠር ነው” ይላል።

በተጨማሪም ለትውልድ የሚተላለፉ ታሪኮችን ለማስተዋወቅ ስዕልን እንደሚያዘወትር ይናገራል።

ከተወሰኑ ዓመታት ወዲህ የሥዕል ሥራዎቹ ላይ ቡናማ ቀለምን በብዛት አካቶ እንደሚሰራ የተናገረው ሠዓሊው፤ ይህም የቡና መገኛ የሆነችው ኢትዮጵያን ለማስተዋወቅ ምክንያት እንደሆነው ይናገራል።

የሥዕል ሥራዎቹን በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ በተለያዩ የአውሮፓ እና ዓለም አቀፍ የስዕል ኤግዚቢሽኖች ላይ ያቀረበ ሲሆን፤  በየመድረኮቹ ላይ የሀገሩን ባህል እና ወግ እንዲሁም ታሪክ ማሳየቱን ነው የሚያስረዳው።

ሠዓሊው በቀጣይ ሥራዎቹን ለሕዝብ ለማድረስ ዝግጅት እያደረገ እንደሆነ እና በተለይ ቡና ተኮር የሆኑ የሥዕል ስራዎቹን ከታሪክ ጋር በማስተሳሰር በቀጣይ ኤግዚቢሽኖች ላይ ለማቅረብ ውጥን እንዳለው ተናግሯል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 1 2018 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!

በኢትዮጵያ ነፃ ኘሬስ ከ25 ዓመት በላይአገልግለናል !!! -የአርበኞች አደራና የትውልዱ...

ከሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የተላለፈ ጥሪ

በክልላችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደገ የመጣው የተሳሳተ ስሌት የወለደው...

በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ በከባድ መሳሪያዎች የታገዘ  የተኩስ ልውውጥ ተካሄደ

ለዓለም የንግድ ሰንሰለት እጅግ ስትራቴጂካዊ በሆነው የሆርሙዝ ባህረ ወሽመጥ...

የሲ.ኤን.ኤን መስራች ቴድ ተርነር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የዓለማችን ግዙፍ የዜና አውታር ሲኤንኤን መስራች ቴድ ተርነር በ87...