ቴአትሩ በዶክተር ተሻለ አሰፋ ተዘጋጅቶ ቀደምትና አዳዲስ ተዋንያንን በመያዝ፣ በድርሰትና በዝግጅት ተሻሽሎ፣ በአዲስ መልክ ከእሑድ ሐምሌ 20 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለዕይታ ሊበቃ እንደሆነ የቴአትሩ ጸሐፊ መልካሙ ዘርይሁን ገልጿል።
ሥድስት ወራት የልምምድ ጊዜ የፈጀው ይህ ታሪካዊ ቴአትር የተዋንያኑን አቅምና ብቃት በሚገባ መፈተን የቻለ እንደነበርም ሰምተናል።
የዛሬ 25 ዓመት በደራሲ መልካሙ ዘርይሁን ተፅፎ በማንያዘዋል እንደሻው የተዘጋጀው ንጉሥ አርማህ ቴአትር ተስፋዬ ገብረሃና እንደ ልዑል፣ ቅድስት ገ/ስላሴ እንደ ልዕልት በመሆን ተጫውተውታል።
ከ25 ዓመታት በኋላም ቴአትሩ ሲመለስ ሁለቱም ተዋንያን ንጉሥና ንግስት ሆነው እንደሚጫወቱ ከደራሲው ሰምተናል።
