የሀዋሳ የቀድሞው ከንቲባ ስለታቸውን አስገቡ ምስክርነትም ሰጡ

Date:

“ቅዱስ ገብርኤል ሆይ አውጣኝ አልኩት ጸሎቴን ሰምቶ አወጣኝ”……”የቀድሞው የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ምስክርነት !!!

የሐዋሳ ከተማ የቀድሞ ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ጸጋዬ ቱኬ በሐሰት በተከሰሱበት የክስ መዝገብ 13 ዓመት ተፈርዶባቸው ወደ ወህኒ ሲወረወሩ በእስር ቤት ሆነው ለቅዱስ ገብርኤል ጸሎት ልመናንን አቀረቡ።

“በአዉደ ምህረትህ ቆሜ ስለክብርህ መስከርያለሁና ለቂርቆስና እየሉጣ የደረስክ ቅዱስ ገብርኤል ሆይ አንተ ድረስልኝ ! የኔ እዉነት ተቀብሮ እንዳይቀር እርዳኝ” ሲል ተለማመኑት።

እነሆ መላእከ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል በግፍ እና በበደል ለተገፉት ፈጥኖ መድረስ ባህሪው ነው እና ሰኔ 12 የዓመቱ ሚካኤል ቀን የባህራንን የሞት ደብዳቤ የሻረ አምላክ ከተፈረደባቸው የ 13 ዓመት የሐሰት እስራት ፍርድ በይግባኝ ነጻ ተብለው በሠላም ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተቀላቀሉ።

እነሆ ድንቅ ታምር ያደረገላቸው እና ጸሎት ልመናቸውን የሰማውን ቅዱስ ገብርኤል በአውደ ምህረት ቆመው ትላንት አመስግነዋል። ስለታቸውንም 5000 ብር አስገብተዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከጂሃድና ከእምቢተኝነት ውጭ ሌላ መንገድ የለም!

የኢራኑ ከፍተኛ መሪ ሞጅተባ ኻመነኢ እሁድ ዕለት በቴሌግራም ገጻቸው...

አሜሪካ እና ኢራን ዳግም ወደ ድርድር ?

ኢራን ከአሜሪካ ጋር በሚደረገው ድርድር ሙሉ በሙሉ እንዳልወጣች፣ ነገር...

እስራኤል በጋዛ በፈፀመችው ጥቃት የሐማስ ከፍተኛ የደኅንነት ባለሥልጣን መገደሉ ተዘገበ

እስራኤል እሁድ ዕለት በጋዛ በፈፀመችው ጥቃት በሐማስ የሚመራው የፍልስጤም...

አሰቃቂውን ጥቃት የፈጸሙ ተጠያቂዎች ለፍትሕ እንዲቀርቡ ፓትርያርኩ ጠየቁ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ፣ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት...