በሰሜን ወሎ መንበረ ጵጵስና ሀገረ ስብከት በተለይ በቆላማ ወረዳዎች ክረምቱ ወቅቱን ጠብቆ ባለመግባቱና የዝናብ እጥረት በመከሰቱ ጸሎተ ምኅላ ታውጇል።
ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ኹሉም ገዳማት፣ አድባራትና አጥቢያ አብያተክርስቲያን ከዛሬ ሐምሌ 20 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለ7 ቀናት የሚቆይ ምኅላ አውጀዋል።
ኹሉም ሕዝበ ክርስቲያን በየአብያተ ክርስቲያናቱ ዘወትር ጠዋት በመገኘት በተሰበረ ልብ ወደ እግዚአብሔር እንድጸልይ ብፁዕነታቸው ትናንት ሐምሌ 19 ቀን 2017 ዓ.ም አባታዊ መልእክት አስተላልፈዋል።
ትናንት አዳሩን በወልዲያ መጠነኛ ዝናብ ቢዘንብም በቆላማው ቀበሌዎች፣ በቆቦ፣በአላማጣ እንዲሁም በራያ አዘቦ እስካሁን ዝናብ እንዳልዘነበ ተሰምቷል፡፡
