ህንድ በዚህ ሳምንት ከአሜሪካ ጋር የምታደርገውን የንግድ ስምምነት ካላጠናቀቀች እስከ 25 በመቶ የሚደርስ ታሪፍ ሊጠብቃት እንደሚችል ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ተናግረዋል።
ለጋዜጠኞች ትራምፕ በሰጡት መግለጫ ኒው ዴሊ ስምምነት ላይ መድረስ ካልቻለችከፍተኛ ታሪፍ ይገጥማት እንደሆነ ሲጠየቁ “አዎ፣ እንደዛ ይመስለኛል” ብለዋል። ዩናይትድ ስቴትስ ህንድ እና ሌሎች በርካታ ሀገራት የንግድ ስምምነት ላይ እንዲደርሱ ወይም ታሪፍ እንዲጤል የኦገስት 1 ቀነ-ገደብ አስቀምጧል።
የህንድ እና የአሜሪካ ባለስልጣናት የንግድ ስምምነት ላለፉት ጥቂት ወራት ሲደራደሩ ቆይተዋል፣ ነገር ግን ባለስልጣናቱ በጥንቃቄ ጉዳዩ እየተመራ መሆኑን ያነሳሉ።
ትራምፕ ከህንድ ጋር ሊያደርጉት ከሚችለው ስምምነት ምን እንደሚጠብቀው ሲጠየቁ “የምናየው ይሆናል ህንድ ጥሩ ጓደኛ ነበረች፤ ነገር ግን ህንድ ከሞላ ጎደል ከማንኛውም ሀገር የበለጠ ታሪፍ ተጥሎባታል” ብለዋል።
በሚያዚያ ወር ላይ ትራምፕ በህንድ ምርቶች ላይ እስከ 27 በመቶ የሚደርስ ታሪፍ አውጀው ነበር ፣ በኋላ ላይ ግን ቆሟል ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ሁለቱም ወገኖች በስምምነት ለመደራደር እየሞከሩ ሲሆን ባለሥልጣናቱ አንዳንድ ጊዜ አዎንታዊ እና በሌላ ጊዜ ደግሞ አስቸጋሪ መሆኑን ገልፀዋል።
“ከህንድ አቻዎቻችን ጋር መነጋገራችንን እንቀጥላለን። ሁልጊዜም ከእነሱ ጋር በጣም ገንቢ ውይይት አድርገናል” ሲሉ የአሜሪካ የንግድ ተወካይ ጄሚሶን ግሬር በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ተናግረዋል።
ግብርና እና የወተት ተዋጽኦዎች ለሁለቱም ሀገራት ቁልፍ ከሆኑ ነጥቦች መካከል ናቸው። ለዓመታት ዋሽንግተን የሕንድ የእርሻ ዘርፍን እንደ ትልቅ ያልተነካ ገበያ በመመልከት የበለጠ ለመድረስ ስትሰራ ቆይታለች።
ነገር ግን ህንድ የምግብ ዋስትናን፣ የኑሮ ሁኔታን እና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ትናንሽ ገበሬዎችን ፍላጎት በመጥቀስ ዘርፉን ዝግ አድርጋ ቆይታለች።ባለፈው ሳምንት የህንድ ንግድ ሚኒስትር ፒዩሽ ጎያል ለሲኤንቢሲ እንደተናገሩት የግብርናው ዘርፍ ለህንድ ውሳኝ ነው እናም የገበሬዎችን ጥቅም “በደንብ እናስጠብቃለን” ሲሉ አረጋግጠዋል።
በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
