በጋዛ እርዳታ እየጠበቁ በነበሩ ተረጂዎችላይ በተከፈተ ተኩስ በጥቂቱ 30 ሰዎች መገደላቸው ተሰማ።
በሐማስ የሚመራው የህዝብ አስተዳደር እንደገለጸው በሰሜናዊ ጋዛ በሚገኘው
ዚኪም ድንበር አቅራቢያ ለእርዳታ በተሰባሰቡ ንጹሃን ላይ የእስራዔልጦር አባላት የተኩስ እሩምታ ከፍተዋል።
በዚህም ከ300 በላይ ሰዎች ሲጎዱ በጥቂቱ 30 ሰዎች ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል
ነው ያለው።
የእስራዔል ጦር በበኩሉ በስፍራው የእርዳታ እህል የጫነ ተሽከርካሪን በከበቡሰዎች ላይ የማስጠንቀቂያ ተኩስ መክፈቱን ጠቅሶ፥ በተኩሱ ስለደረሰው ጥቃት ግን ምንም የሚያውቀው ነገር እንደሌለ ገልጿል።
በአንጻሩ እስራዔል በስፍራው ስለደረሰው ጉዳት እያጣራሁ ነው ብላለች።
በጋዛ የሚገኘው የአል-ሺፋ ሆስፒታል ዳይሬክተር ሞሃመድ አቡ ሳልሚያ በበኩላቸው እስካሁን የ35 ሰዎች አስከሬን
ተቀብለናል ብለዋል።
ዘግየት ብሎ የወጣ የአሶሺየትድ ፕረስ ዘገባ ደግሞ ሆስፒታሉ 45 ሰዎችእንደተገደሉ መግለጹን አስነብቧል።
