ብሔራዊ ባንክ በ2017 ከትግራይ 189 ኩንታል፣ ከአፋር ደግሞ 225 ኪሎ ግራም ወርቅ መግዛቱ ተገለጸ

Date:

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በተጠናቀቀው የ2017 በጀት ዓመት ከትግራይ ክልል 189 ኩንታል ወርቅ፣ ከአፋር ክልል ደግሞ 225 ኪሎ ግራም ወርቅ ግዢ መፈጸሙ ተገለጸ።

የትግራይ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 189 ኩንታል ወርቅ ለብሔራዊ ባንከ በማስገባት ከ250 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን የክልሉ ማዕድን ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ተስፋዓለም ሀድጉ አስታውቀዋል።

በተመሳሳይ ከአፋር ክልል ወደ ብሄራዊ ባንክ 225 ኪሎ ግራም ወርቅ መቅረቡን ክልሉ አስታውቋል፤ ወደ ባንኩ የሚገባው የወርቅ መጠን በእጥፍ መጨመሩን የክልሉ ማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊአብዱል ኢንድሪስ ገልጸዋል።

በ2016 በጀት ዓመት 96 ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ መግባቱን ያስታወሱት ምክትል ኃላፊው በተጠናቀቀው 2017 በጀት ዓመትይህ ቁጥር ወደ 225 ኪሎ ግራም ወርቅ ማሳደግ እንደተቻለ መግለጻቸውን ከፕረስ ድርጅት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በ2017 በጀት ዓመት ወደ ብሔራዊ ባንክ 4ሺህ 700 ኪሎ ግራም ወርቅ ማስገባቱን የክልሉ ማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ ማስታወቁን መዘገባችን ይታወሳል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...

አገር እንዲህ ዓይንህን ለአፈር ይባላል?

በተጀመረው የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ መሸነፏን ተከትሎ አፍሪካ...

አሜሪካ እና ኢራን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በ24 ሰዓት ውስጥ እንደሚፈራረሙ ፓኪስታን አስታወቀች

ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በሰላም ድርድሩ ማዕቀፎች ላይ መስማማታቸውን...