በየመን  ሕገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ላይ ዘመቻ መጀመሯ ተሰምቷል

Date:

በድርጊቱ በሚሳተፉ ላይ ጥብቅ እርምጃ ይወሰዳል ተብሏል።

በቅርቡ በደቡብ አቢያን ግዛት ጀልባ ሰጥሞ ከ90 በላይ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች መሞታቸውን ተከትሎ፤ አፍሪካውያን ስደተኞችን በሀገሪቱ በኩል የሚያንቀሳቅሱ ሕገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ላይ ዘመቻ መጀመራቸውን የየመን ባለሥልጣናት ከትላንት በስቲያ ረቡዕ  አስታውቀዋል፡፡

የአቢያን ግዛት ፖሊስ ባወጣው መግለጫ፤ “የአፍሪካ ዜግነት ያላቸውን ፍልሰተኞችና ስደተኞችን በማጓጓዝ ወይም በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ላይ ተሳትፎ የተገኘ የትኛውም አካል ላይ ጥብቅ እርምጃ ይወሰዳል” ብሏል፡፡

በአዲሱ እርምጃ መሠረት፤ የፀጥታ ኃይሎች በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር አገልግሎት ላይ የሚውሉ ተሽከርካሪዎች፣ ጀልባዎችና ሌሎች የመጓጓዣ ዘዴዎች እንደሚወረሱ ተጠቁሟል።
መረጃው የስፑትኒክ ኢትዮጵያ ነው።፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...