አለርት ሆስፒታል የሕፃናት ዓይን ህክምና ማዕከል ሥራ ጀመረ

Date:

አለርት ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የህፃናት ዓይን ህክምና ማዕከል ስራ አስጀምሯል። ማዕከሉ በህፃናት ላይ የሚደርስ ዓይነ ስውርነትን በመከላከል ረገድ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ነው ተብሎለታል።

በማዕከሉ የምርቃት መርሃግብር ላይ የተገኙት የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ፤ በሕፃናት ላይ የሚደርስ ዓይነ ስውርነትና የዓይን ጤና ህመም ከህፃናቱ ባለፈ ወላጅ ላይ፣ ማኅበረሰቡ እና ሀገር ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድር መሆኑን አንስተዋል።

ማዕከሉም የተሞላ የዓይን ህክምና በመስጠት የመማር፣ ማንበብ፣ መጫወት በአጠቃላይ ለህፃናቱ ከእይታ ባለፈ የወደፊት ተስፋ የሚሰጥ መሆኑን ገልፀዋል።

40 በመቶ የሚሆነው የሀገሪቱ የህዝብ ቁጥር ህፃናት መሆናቸውን ገልፀው፤ ዛሬ ላይ በህፃናት ላይ የሚሰራ ስራ ለነገ ሀገር እድገትና ብልፅግና የማይተካ ሚና ያለው መሆኑን አስታውቀዋል።

ማዕከሉም በህፃናት ላይ የሚደርስ የዓይነ ስውርነትና የዓይን ህመምን በመከላከል ረገድ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ነው ብለዋል።

የአለርት ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ ዶክተር ሽመልስ ገዛህኝ በበኩላቸው፤ ሆስፒታሉ የተሟላ ግብአትና ብቁ ባለሙያዋችን በመጠቀም ጥራቱን የጠበቀ የህፃናት የዓይን ህክምና በመስጠት በህፃናት ላይ የሚደርስ የዓይን ጤና እክልንና ብርሀንን በመመለስ የወደፊት ተስፋ የሚሰጥ መሆኑን ገልፀዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...