እስራኤል”የሃማስን ቃል አቀባይ አቡ ዖቤይዳን ገድያለሁ” አለች።የሃማስ ወታደራዊ ክንፍ ቃል አቀባይ አቡ ዖቤይዳ በእስራኤል አየር ጥቃት ጋዛ ከተማ ውስጥ ህይወታቸውን እንዳጡ አይ ዲ ኤፍ አስታውቋል።
የእስራኤሉ መከላከያ ሚኒስትር፣ እስራኤል ካትዝ ጦራቸውን አመስግነው ጠላቶቻችንን ቴል አቪቭ ዒላማ ውስጥ ማስገባቷን ትቀጥልበታለች ብለዋል።
የእስራኤልን የአገር ውስጥ ደህንነት መስሪያ ቤትን ሺንቤትንም አድንቀዋል ካትዝ። በመካከለኛው ምስራቅ የእስራኤል ጠላቶች ይጠፋሉ በሚል በተደጋጋሚ ሀሳብ በመስጠትም ይታወቃሉ ሚኒስትሩ ።
ያም ሆኖ ግን ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ ሃማስ በጉዳዩ ላይ ያለው ነገር የለም። ሃማስ ጥቃቱ ደረሰበት በተባለው ስፍራ በርካታ ንጹሃን ሰዎች ማለቃቸውን ከማሳወቁ ውጭ በቃል አቀባዩ ህልፈት ዙሪያ ማብራሪያ አልሰጠም።
ጥቃቱ በጋዛ ያለው ሰቆቃ ከባድ እየሆነ መምጣቱንም ያሳያል ተብሏል ።በጋዛ 63,459 ሰዎች ህይወታቸውን ሲያጡ 160,256 የሚሆኑት ደግሞ ቆሰዋል።
ዘገባው የ ዘ ጀሩሳሌም ፖስት እና አልጀዚራ ነው።
