መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ማዕከል

Date:



መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በተለያዩ ተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶች ወደ አንድ ማዕከል በማምጣት ቀልጠፋ እና ምቹ አገልግሎት ለመስጠት ወደ ሥራ የገባ ማዕከል ነው፡፡

በማዕከሉ አገልግሎት እየሰጡ ከሚገኙ ተቋማት መካከል አንዱ የሆነው የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የውጭ ሀገር ዜጎች የሥራ ፍቃድ እና የዲጂታል ኢንተርፕራይዝ ምስረታ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

ከሥራ ፍቃድ አገልግሎቱ በተጨማሪ  በማዕከሉ የሥራ ፍቃድ ማደስ፣ የሥራ ፈቃድ መተካት እና የሥራ ፈቃድ ክሊራንስ እየተሰጠም ይገኛል፡፡

በሚኒስቴሩ ብቻ እየተሰጠ የነበረው አገልግሎት በመሶብ የአንድ ማዕክል አገልግሎት በተጨማሪነት መሰጠቱ የሥራ ጫና በመቀነስ ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት እንዳስቻለ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሀገር ውስጥ ሥራ ሥምሪት ማስፋፊያ ዴስክ ኃላፊ አቶ ደጀኔ በቀለ ገልጸዋል፡፡

ዜጎች አገልግሎቱን በሚኒስቴሩ ወይም በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከል ቀርበው ባጠረ ጊዜ ማግኘት እንደሚችሉም ጠቁመዋል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ በከባድ መሳሪያዎች የታገዘ  የተኩስ ልውውጥ ተካሄደ

ለዓለም የንግድ ሰንሰለት እጅግ ስትራቴጂካዊ በሆነው የሆርሙዝ ባህረ ወሽመጥ...

የሲ.ኤን.ኤን መስራች ቴድ ተርነር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የዓለማችን ግዙፍ የዜና አውታር ሲኤንኤን መስራች ቴድ ተርነር በ87...

የኢትዮጵያ አጠቃላይ ብድር 51.8 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ይፋ ሆኗል

ኢትዮጵያ  በድጋፍ መልክ ከአሜሪካ በየዓመቱ  በመንግስት በኩል ፈሰስ የሚደረግ...

ከ8 ሺህ በላይ ጥንታዊ የብራና ጽሑፎችን እና ሰነዶችን ወደ ዲጂታል ተቀየሩ

የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብት እና ቤተ መጽሐፍት አገልግሎት ከተለያዩ ተቋማት፣...