የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአዲስ ዓመት በዓል ምክንያት በማድረግ በሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ እየተገነባ ለሚገኘው አስኮ የመጀመርያ ደረጃ ሆስፒታል ግንባታ 15,000,000 (አስራ አምስት ሚልዮን) ብር የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል።
የገንዘብ ድጋፉን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ ፣ የንግድ ባንክ ስራ አመራር አባላት ለሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ ሲ/ር ዘቢደር ዘውዴ አሰረክበዋል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የስራ አመራሮች በሙሉ ስላደረጋችሁት መልካም ተግባር ሁሉ በህፃናቱ እና አረጋዊያኑ ስም ከልብ እናመሰግናለን።
ሜሪጆይኢትዮጵያ
ኢትዮጵያዊያን_ለኢትዮጵያዊያን
“ሁሌም ስሰጥ የምቀበለው አለ”
